የኮቪድ-19 ክትባት ለጤና እንክብካቤ ሰጪዎች
针对看护人的 COVID-19 疫苗接种 |Tiêm Vắc-Xin COVID-19 cho Chăm Sóc Viên | Tallaalada COVID-19 ee loogu talagalay Daryeel Bixiyeyaasha |Вакцинация от COVID-19 для помощников| 간병인을 위한 COVID-19 백신 접종 | لقاحات كوفيد-19 لمزودي الرعاية |Vacunas contra el COVID-19 para los cuidadores
ሁሉም የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች ነጻ
እና ለደኅንነት አስተማማኝ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለመከተብ ብቁ ናቸው
“ሁሉም የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን በነጻ አሁኑኑ ለመከተብ ብቁ ናቸው። ሁሉም የጤና ክብካቤ ሰጪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን በነጻ አሁኑኑ ለመከተብ ብቁ ናቸው።
ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው እናም የዋሽንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት (DOH) በሚችሉት ፍጥነት ክትባት እንዲወስዱ ይመክራል። በ U.S. ብቻ ክትባት የወሰዱ ከ 50 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ይቀላቀላሉ።
ክትባት ለመውሰድ፣ በአቅራቢያዎ ያለን ቦታ መፈለግ እና ቀጠሮ ማስያዝ አለብዎት።
ቀጠሮ ያስይዙ
ነጻ ክትባት በብዙ ቦታዎች ይገኛል። ነጻ ክትባቱን ለመከተብ የጤና እንክብካቤ የመድን ሽፋን እንዲኖርዎት አይገደዱም።
የDOH የክትባት ቦታ አመልካቸ ድረገጽን በመጎብኘት ለእርስዎ የሚቀርብዎትን የክትባት ቦታ ያግኙ። በመረጡት የክትባት ቦታ የክትባት ቀጠሮን ለማስያዝ መመሪያዎቹን ይከተሉ።
የካይዘር ፐርማነንቴ የጤና ሽፋን ካልዎት እና ወደ ካይዘር ማእከል መሄድ ከፈለጉ፣ ለካይዘር ፐርማነንቴ ዋሺንግተን (KPWA) ወይም ለካይዘር ፐርማነንቴ ሰሜን ምእራብ (KPNW፣ በክላርክ ወይም ኮውሊትዝ ካውንቲዎች ለሚኖሩ)እንዚህን ደረጃዎች ይከተሉ።
በፐጌት ሳውንድ ወይም ስፖኬን ውስጥ የ KPWA ሽፋን ካልዎት:
- ወደ አካውንትዎ ይግቡ እና በ "E-visit" አማካኝነት ቀጠሮ ይያዙ።
- የዳሰሳ ጥናቱን ለመሙላት ወደ KPWA በመለያ መግባት ያስፈልግዎታል። በ KPWA የመሥመር ላይ (ኦንላይን) መለያ ካልፈጠሩ፣ እነዚህን መመሪያዎች ይከተሉ።
- ወደ 1-800-352-3610 ይደውሉ።
- ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ውጭ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ከሆነ እና የትርጉም አገልግሎቶችን ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ወይም በመሥመር ላይ መለያ መፍጠር የማይችሉ ከሆነ ይህን አማራጭ ይጠቀሙ።
በፐጌት ሳውንድ ወይም ስፖኬን ውስጥ የ KPWA ሽፋን ካልዎት:
- ወደ kp.org/appointments ይሂዱ ወይም የ Kaiser Permanente መተግበሪያን ይጠቀሙ።
- ወደ 1-800-813-2000 ይደውሉ።
- ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ውጭ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ከሆነ እና የትርጉም አገልግሎቶችን ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ወይም በመሥመር ላይ መለያ መፍጠር የማይችሉ ከሆነ ይህን አማራጭ ይጠቀሙ።
ስለ ክትባት ጥያቄ አልዎት?
ሌላ ጥያቄ ቢኖረኝስ?
እንዴት ሁለቱም ክትባቶች እንደሚሠሩ፣ በተለያዩ ደረጃ ላይ የተለያዩ ሰዎች ብቁነትን እና ብዙ ሌሎችን ጨምሮ በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች የዋሽንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት (DOH) አጠቃላይ ድረገጽን ይመልከቱ።
በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ብዙ መልሶችን ከበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከል (CDC) ማየት ይችላሉ።
እኔ አሁን ኮቪድ -19 አለብኝ። ክትባት ያስፈልገኛል?
አዎ። ባለሙያዎች ከበሽታው ካገገሙ በኋላ ለምን ያክል ጊዜ እንደገና ከመታመም እንደተጠበቁ አሁንም ስላላወቁ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከል (CDC) ከዚህ ቀደም ኮቪድ-19 ቢኖርብዎትም ክትባት እንዲወስዱ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።
ሙሉ ክትባቱን ከወሰድኩ በኋላ አሁንም PPE ማድረግ እና ማህበራዊ ርቀት መጠበቅ አለብኝ?
በዚህ ሀሳብ ላይ የCDC መመሪያዎችን ይመልከቱ። በብዙ አጋጣሚዎች፣ የሰዎች ቁጥርን እና በአካባቢዎ ያሉት በሙሉ ተከትበዋል ወይ የሚለውን መሰረት በማድረግ፣ አሁንም PPE ማድረግ እና ማህበራዊ ርቀት መጠበቅ አለብዎት
ክትባይ የት ማግኘት እችላለው?
ክትባት ለማግኘት ብዙ ቦታዎች አሉ። የክትባት ቦታ መረጃን ይመልከቱ።
ደንበኛዬ ክትባት የት ማግኘት ይችላል?
ደንበኛዎ አሁን ክትባት ማግኘት ይችላል። ከማርች 17 ጀምሮ አብዛኛዎቹ ደንበኞች ብቁ ናቸው እና ከኤፕሪል 15 ወዲህ ደግሞ ከ16 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቁ ናቸው።
እስካሁን ስንት እንክብካቤ ሰጪዎች ክትባት ወስደዋል?
በ U.S ብቻ ከ200 ሚሊዩን ዶዞች በላይ የተሰጡ ሲሆን ፣ከነዛ ውስጥ ብዙ ሺህዎች ለእንክብካቤ ሰጪዎች የተሰጠ ነው። ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ እንክብካቤ ሰጪዎችን ያጠቃልላል። በአሁኑ ሰአት ዩናይትድ ስቴትስን ውስጥ እና አለም ላይ ያለውን ውሂብ ለማየት የጆን ሆፕኪንስን ዩኒቨርሲቲ የክትባት መመዝገቢያን ይመልከቱ።
ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላል?
ክትባቱን የወሰዱ የተወሰኑ ሰዎች ድካም ወይም ትኩሳት የመሳሰሉ ተጓዳኝ ጉዳቶች ያጋጥማቸዋል። የክትባቱ ተጓዳኝ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ ትንሽ፣ ጊዜያዊ እና ከ1-2 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚጠፉ ናቸው። ክትባቱ እየሰራ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።
ክትባት መውሰድ ምን ይመስላል?
የእርስዎ ጉብኝት ከመደበኛ የዶክተር ጉብኝት በጣም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፤ ቀጠሮዎ በያዙበት ቦታ መሰረት፣ በትልቅ ህዝባዊ ቦታ ውስጥ የጅምላ መከተቢያ ክሊኒክ ላይ ሊሆን ይችላል፤ ወይም መኪናዎ ውስጥ የሚቆዩበት እየነዱ የሚከተቡበት ክሊኒክም ሊሆን ይችላል። የማንነት ቅጽ ሊጠየቁ ይቻላሉ። የኮቪድ -19 ክትባትን መከተብ፣ በላይኛው ክንድዎ ላይ የሚወጉበት፣ እንደሌሎች ክትባቶች ወይም መርፌዎች ነው። የአለርጂ ግብረ መልስ እንደሌልዎት እርግጠኛ ለመሆን መርፌ ከተወጉ በኋላ በትንሹ 15 ደቂቃ እንዲቆዩ ይጠየቃሉ።
ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?
አዎ፣ ለሰዎች የሚሰጠው የኮቪድ-19 ክትባቶች ደህንነቱን የጠበቀ እና ውጤታማ ነው። እንደ ሌሎች ክትባቶች ፣ በጥብቅ እና ደህንነቱን በጠበቀ የክሊኒክ ፕሮቶኮሎችን በመጠቀም የተሰሩ ናቸው። የክትባቱን ጥቅም በቅርበት መታየቱ ቀጥሏል። ስለ ክትባቱ ደህነት የበለጠ ይማሩ።
ክትባቱ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ነጻ ነውን?
አዎ። ለሁሉም ነጻ ነው፤ ያልዎት የጤና ሽፋን ምንም ቢሆን፣ ወይም የጤና ሽፋን ባይኖርዎትም ችግር የለውም።
ብቁነት
ከማርች 31፣ 2021 ጀምሮ፣ የዋሽንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት (DOH) የክትባት ብቁነት ማስረጃን አይጠይቅም። ቀጠሮ በሚይዙበት ጊዜ እና ክትባት በሚወስዱበት ጊዜ ፣የብቁነት ማስረጃ አይጠየቁም።
የክትባት ምንጮች
ጥያቄዎች?
ስለ ክትባቱ ጥያቄዎች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎ ወደ 1-877-606-6705 ይደውሉ። ከፍተኛ የስልክ ጥሪዎችን እያስተናገዱ ስለሆነ እና እርስዎን ሊያግዝዎት ላይችሉ ስለሚችሉ እባክዎ እባክዎ Member Resource Center (MRC) ን አያነጋግሩ።