የቋንቋ ድጋፍ

Ver en español | 查看中文 | 한국어로 보기 | Посмотреть на русском | Xem bằng tiếng việt | عربى | Soomaali

ሙሉ በሙሉ የተተረጎሙ ኮርሶች ለእርስዎ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የመማሪያ ልምዶችን ተሞክሮ ይሰጣሉ።

እንግሊዘኛ አቀላጥፈው ቢናገሩም ወይም እንግሊዘኛ ለመማር ቢፈልጉም እንኳ፣ እርስዎን ለስኬት ለማዘጋጀትና እንደ ተንከባካቢ በቅልጥፍና እንዲሰሩ በእርስዎ ተቀዳሚ ቋንቋ የሚሰጠው ኮርስ የተሻለ ሊሆን ይችላል።

የአባል የመርጃ ማዕከል (MRC) ለመመዝገብ ሲደውሉ በሚመርጡ ቋንቋዎች በአቅራቢያዎ መሰረታዊ የስልጠና ወይም ቀጣይነት ያለው ትምህርት (CE) ኮርሶችን እንዲያገኙ ያግዝዎታል። ለMRC በ 1-866-371-3200፣ ከ8 am እስከ 4:30 p.m. ከሰኞ እስከ አርብ ይደውሉ። ወይም በ mrc@myseiubenefits.org ኢሜይል ያድርጉ።

ስለ የቋንቋ ድጋፍ አማራጮች ድጋፍ የበለጠ ይወቁ፦

መሰረታዊ ስልጠና ኮርሶች

ሙሉ በሙሉ የተተረጎመ መሰረታዊ ስልጠና ኮርሶች እስከ 9 በሚደርሱ የተለያዩ ቋንቋዎች እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ሊገኙ ይችላሉ። በአቅራቢያዎ የሚገኙ ኮርሶች ከሌሉ ባለሙያ አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ።

ቋንቋዎቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ስፓንኛ
  • ራሺያኛ
  • ካንቶኒዝ
  • አረብኛ
  • አማርኛ
  • ኮሪያኛ
  • ቪትናሚኛ
  • ካምቦዲያኛ
  • ሶማሊኛ

የእንግሊዝኛ መሰረታዊ ስልጠና ኮርስን ከአስተርጓሚ ጋር እየወሰዱ ከሆነ፣ የተተረጎሙ የኮርስ ማቴሪያሎች በሚከተለው ሊቀርቡ ይችላሉ፦

  • አማርኛ
  • ኔፓሊ
  • ሳሞአን
  • ታጋሎግ
  • ዩክሬንኛ
  • ላኦሺያን
  • ፋርሲ
  • ፑንጃቢ

ከእነዚህ ቋንቋዎች ውስጥ አንዱን በዋናነት የሚናገሩ ከሆነ፣ ለክፍሉ አስተርጓሚ ያስፈልግዎታል፣ ነገር ግን አንዳንድ ማቴሪያሎችን በራስዎ ቋንቋ ይቀበላሉ።

ነፃ የባለሙያ አስተርጓሚ ይጠይቁ

በአቅራቢያዎ በ50 ማይል ክልል ውስጥ በአካል በፈለጉት ቋንቋ መሰረታዊ ስልጠና ኮርሶች ካልተገኙ፣ ነፃ ባለሙያ አስተርጓሚ ለመጠየቅ፣ ለአባል የመርጃ ማዕከል (MRC) በ1-866-371-3200፣ ከ8 a.m. እስከ 4:30 p.m.፣ ከሰኞ እስከ አርብ ይደውሉ። ወይም በ mrc@myseiubenefits.org ኢሜይል ያድርጉ።

እርስዎ ወይም አሰሪዎ መሰረታዊ ስልጠናዎ ከሚጀምርበት ቀን ከ3-4 ሳምንታት በፊት የአስተርጓሚውን ጥያቄ ማቅረብ አለባችሁ።

CE ኮርሶች

ሁሉም መደበኛ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ረዳቶች (HCAs) እና የአዋቂ ልጆች አቅራቢዎች ከልደት ቀናቸው በፊት በየዓመቱ 12 CE ክሬዲቶችን ማጠናቀቅ መቻል አለባቸው

CEsን እያጠናቀቁ ከሆነ፣ 2 የተለያዩ የአስተርጓሚ አማራጮች ይኖሩዎታል፦

  • ባለሙያ አስተርጓሚዎች።
  • የማህበረሰብ አስተርጓሚዎች።

ባለሙያ አስተርጓሚዎች።

አንዳንድ የዌቢናር እና በአካል አስተማሪ-መር CE ኮርሶች በመረጡት ቋንቋ ሊሰጡ ይችላሉ። እነዚህን ኮርሶች ለማግኘትና ለመመዝገብ ወደ MRC መደወል ይችላሉ። ምን አይነት ክፍሎች እንዳሉ እነሱ ሊያሳውቁዎት ይችላሉ።

በመረጡት ቋንቋ ምንም በአካል የቀረቡ CEs ወይም ዌብናሮች ከሌሉ፣ MRC ነፃ የባለሙያ አስተርጓሚ ጠይቀው ሊረዳዎት ይችላል።

በአካል ለሚሰጡ ኮርሶች ባለሙያ አስተርጓሚ መጠየቅ

ሁሉም ባለሙያ አስተርጓሚ ጥያቄዎች በMRC በኩል መቅረብ አለባቸው። ለመመዝገብ እና የቋንቋ ድጋፍ ለመጠየቅ ወደ MRC በ 1-866-371-3200 ይደውሉ ወይም በ mrc@myseiubenefits.org ኢሜይል ይላኩ። እነሱ ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ 8 a.m. እስከ 4:30 p.m. ይገኛሉ።

የማህበረሰብ አስተርጓሚ

ለዌብናሮች እና የኦንላይ CEs የማህበረሰብ አስተርጓሚ መጠቀም ይችላሉ። የማህበረሰብ አስተርጓሚ ማለት ደንበኛዎ ያልሆነ እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ጓደኛ ወይም ዘመድ ነው።

ለኦንላይን CEs፣ የማህበረሰብ አስተርጓሚ እንደሚጠቀሙ ለMRC ማሳወቅ አያስፈልግዎትም። በኦንላይን CE ውስጥ እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ይወቁ

የማህበረሰብ አስተርጓሚ ጥያቄዎች ለዌብናሮች

ለቀጥታ፣ በአስተማሪ-መር ዌብናሮች፣ በኮርሱ ወቅት የሚረዳዎት የማህበረሰብ አስተርጓሚ እንዳለዎት ለMRC ማሳወቅ አለብዎት። ክፍሉ መቼ እንደሚካሄድ ለአስተርጓሚው የመንገር ሃላፊነት የእርስዎ ነው።

ሲመዘገቡ ወይም በዌቢናር ውስጥ ከተመዘገቡ በኋላ ለMRC ማሳወቅ ይችላሉ። ለMRC በ 1-866-371-3200፣ ከ8 am እስከ 4:30 p.m. ከሰኞ እስከ አርብ ይደውሉ። ወይም በ mrc@myseiubenefits.org ኢሜይል ያድርጉ።

ለስልጠና ወይም ለጤና ጥቅሞች የቋንቋ ድጋፍ ይፈልጋሉ?

በ 1-866-371-3200 ወደ MRC ይደውሉ ወይም ከታች ያነጋግሩን እና ተወካይ በቋንቋዎ ጥያቄዎን ይመልሳል።

• አረብኛ
• ካንቶኒዝ
• ካምቦዲያኛ
• ኮሪያኛ
• ሶማሊኛ
• ላኦሺያን
• ስፓንኛ
• ሳሞአን
• ራሺያኛ
• ታጋሎግ
• ዩክሬንኛ
• ቪትናሚኛ

የቋንቋ ምርጫዎን ይለውጡ

የቋንቋ ምርጫዎችዎን በእኔ ጥቅሞች ውስጥ መለወጥ ከፈለጉ፣ MRCን በ 1-866-371-3200 ያነጋግሩ ወይም MRC@myseiubenefits.org ኢሜይል ያድርጉ።