የኮቪድ-19 ክትባት ለጤና እንክብካቤ ሰጪዎች
针对看护人的 COVID-19 疫苗接种 |Tiêm Vắc-Xin COVID-19 cho Chăm Sóc Viên | Tallaalada COVID-19 ee loogu talagalay Daryeel Bixiyeyaasha |Вакцинация от COVID-19 для помощников| 간병인을 위한 COVID-19 백신 접종 | لقاحات كوفيد-19 لمزودي الرعاية |የኮቪድ-19 ክትባት ለጤና ክብካቤ ሰጪዎች |Vacunas contra el COVID-19 para los cuidadores
ሁሉም ተንከባካቢዎች ደህንነቱ ለተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባቶች እና ማበረታቻዎች ብቁ ናቸው።
ሁሉም የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች የኮቪድ-19 ክትባት እና ማበረታቻን በነጻ አሁኑኑ ለመከተብ ብቁ ናቸው።
ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው እናም የዋሽንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት (DOH) በሚችሉት ፍጥነት ክትባት እንዲወስዱ ይመክራል። በ U.S. ብቻ ክትባት የወሰዱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ይቀላቀላሉ።
ክትባት ለመውሰድ፣ በአቅራቢያዎ ያለን ቦታ መፈለግ እና ቀጠሮ ማስያዝ አለብዎት።
ቀጠሮ ያሲዙ
ክትባትዎን ወይም ማበረታቻዎን ለማግኘት ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ያድርጉ፦
- vaccines.govን ይጎብኙ።
- ወደ 1-800-232-0233 ይደውሉ።
- ዚፕ ኮድዎን ወደ 438829 ይላኩ።
ስለ ክትባት ጥያቄዎች አሉዎት?
ሌላ ጥያቄ ቢኖረኝስ?
እንዴት ሁለቱም ክትባቶች እንደሚሠሩ፣ በተለያዩ ደረጃ ላይ የተለያዩ ሰዎች ብቁነትን እና ብዙ ሌሎችን ጨምሮ በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች የዋሽንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት (DOH) አጠቃላይ ድረገጽን ይመልከቱ።
በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ብዙ መልሶችንከበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከል (CDC) ማየት ይችላሉ።
እኔ አሁን ኮቪድ -19 አለብኝ። ክትባት ያስፈልገኛል?
አዎ። ባለሙያዎች ከበሽታው ካገገሙ በኋላ ለምን ያክል ጊዜ እንደገና ከመታመም እንደተጠበቁ አሁንም ስላላወቁ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከል (CDC) ከዚህ ቀደም ኮቪድ-19 ቢኖርብዎትም ክትባት እንዲወስዱ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።
ሙሉ ክትባቱን ከወሰድኩ በኋላ አሁንም PPE ማድረግ እና ማህበራዊ ርቀት መጠበቅ አለብኝ?
በዚህ ሀሳብ ላይ የCDC መመሪያዎችን ይመልከቱ። በብዙ አጋጣሚዎች፣ የሰዎች ቁጥርን እና በአካባቢዎ ያሉት በሙሉ ተከትበዋል ወይ የሚለውን መሰረት በማድረግ፣ አሁንም PPE ማድረግ እና ማህበራዊ ርቀት መጠበቅ አለብዎት።
ክትባይ የት ማግኘት እችላለው?
ክትባት ለማግኘት ብዙ ቦታዎች አሉ። የክትባት ቦታ መረጃን ይመልከቱ።
ደንበኛዬ ክትባት የት ማግኘት ይችላል?
ደንበኛዎ አሁን ክትባት ማግኘት ይችላል። ከማርች 17 ጀምሮ አብዛኛዎቹ ደንበኞች ብቁ ናቸው እና ከኤፕሪል 15 ወዲህ ደግሞ ከ16 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቁ ናቸው።
እስካሁን ስንት እንክብካቤ ሰጪዎች ክትባት ወስደዋል?
በ U.S ብቻ ከ200 ሚሊዩን ዶዞች በላይ የተሰጡ ሲሆን ፣ከነዛ ውስጥ ብዙ ሺህዎች ለእንክብካቤ ሰጪዎች የተሰጠ ነው። ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ እንክብካቤ ሰጪዎችን ያጠቃልላል። በአሁኑ ሰአት ዩናይትድ ስቴትስን ውስጥ እና አለም ላይ ያለውን ውሂብ ለማየት የጆን ሆፕኪንስን ዩኒቨርሲቲ የክትባት መመዝገቢያን ይመልከቱ።
ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላል?
ክትባቱን የወሰዱ የተወሰኑ ሰዎች ድካም ወይም ትኩሳት የመሳሰሉ ተጓዳኝ ጉዳቶች ያጋጥማቸዋል። የክትባቱ ተጓዳኝ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ ትንሽ፣ ጊዜያዊ እና ከ1-2 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚጠፉ ናቸው። ክትባቱ እየሰራ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።
ክትባት መውሰድ ምን ይመስላል?
የእርስዎ ጉብኝት ከመደበኛ የዶክተር ጉብኝት በጣም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፤ ቀጠሮዎ በያዙበት ቦታ መሰረት፣ በትልቅ ህዝባዊ ቦታ ውስጥ የጅምላ መከተቢያ ክሊኒክ ላይ ሊሆን ይችላል፤ ወይም መኪናዎ ውስጥ የሚቆዩበት እየነዱ የሚከተቡበት ክሊኒክም ሊሆን ይችላል። የማንነት ቅጽ ሊጠየቁ ይቻላሉ። የኮቪድ -19 ክትባትን መከተብ፣ በላይኛው ክንድዎ ላይ የሚወጉበት፣ እንደሌሎች ክትባቶች ወይም መርፌዎች ነው። የአለርጂ ግብረ መልስ እንደሌልዎት እርግጠኛ ለመሆን መርፌ ከተወጉ በኋላ በትንሹ 15 ደቂቃ እንዲቆዩ ይጠየቃሉ።
ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?
አዎ፣ ለሰዎች የሚሰጠው የ COVID-19 ክትባቶች ደህንነቱን የጠበቀ እና ውጤታማ ነው። እንደ ሌሎች ክትባቶች፣ ጥብቅ በሆነ የክሊኒካል ሙከራዎች እና በደህነት የማስጠበቅ መመሪያዎች የዳበሩ ናቸው። የክትባት ጥቅሞች በቀጣይነት በቅርበት ይመረመራሉ። ስለ ክትባቱ ደህነት የበለጠ ይማሩ።
የመድኃኒቱ ወጪ ስንት ነው?
እባክዎ ለበለጠ መረጃ የህክምና አገልግሎት አቅራቢዎን ያነጋግሩ።
የክትባት ምንጮች
ጥያቄዎች አሉዎት?
ስለ ክትባቱ ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎ ወደ 1-877-606-6705 ይደውሉ። ከፍተኛ የስልክ ጥሪዎችን እያስተናገዱ ስለሆነ እና እርስዎን ሊያግዝዎት ላይችሉ ስለሚችሉ እባክዎ እባክዎ Member Resource Center (MRC) ን አያነጋግሩ።