የስልጠና የቀን መቁጠሪያ
የስልጠና ክፍሎች አሁን በመላው ዋሽንግተን ስቴት ይገኛሉ።
በአቅራቢያዎ ያሉ ኮርሶች የሚጀምሩበትን እና የሚያበቃበትን ቀን ለማየት፣ ከዚህ በታች ያለውን ስልጠናዎን ይምረጡ እና ቦታውን ጠቅ ያድርጉ።
የግለሰብ አቅራቢዎች (IPs) ለአባላት ግብዓት ማዕከል በ 1-866-371-3200 ከሰኞ-አርብ፣ ከ8:00 a.m. እስከ 4:30 p.m. በመደወል መመዝገብ ይችላሉ። ሲደውሉ፣ ከሚከተለው መረጃዎ ጋር መልዕክት ያስቀምጣሉ፦
- የመጀመሪያ እና የአያት ስም።
- ስልክ ቁጥር።
- መልሶ ለመደወል ምርጥ ጊዜ።
- መመዝገብ የሚፈልጉበት ስልጠና እና ቦታው።
የምዝገባ ቡድን አባል ጥሪዎን ይመልሳል እናም በተቻለ ፍጥነት እንዲመዘገቡ ያግዝዎታል።
የኤጀንሲ አገልግሎት አቅራቢዎች (APs) አሰሪያቸው ጋር በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።

መሰረታዊ ስልጠና 70 ደንበኞችን በከፊልም ሆነ በሙሉ ጊዜ ተንከባካቢ መደበኛ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ረዳቶች (HCAs) ስልጠና ያስፈልጋል።
ያሉትን ኮርሶች የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ቀኖች ለማየት በአካባቢዎቹ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
አካባቢ | ከተሞች |
---|---|
ምስራቃዊ ዋሽንግተን | Clarkston፣ Colville፣ Ellensburg፣ Richland፣ Spokane፣ Walla Walla |
Puget Sound | Arlington፣ Bellevue፣ Bellingham፣ Des Moines፣ Everett፣ Kent፣ Lakewood፣ Lynnwood፣ Mount Vernon፣ Puyallup፣ Seattle፣ Tukwila |
ማዕከላዊ ዋሽንግተን | Moses Lake፣ Omak፣ Wenatchee፣ Yakima |
ደቡብ ምዕራብ ዋሽንግተን | Aberdeen፣ Bremerton፣ Chehalis፣ Lacey፣ Longview፣ Oak Harbor፣ Olympia፣ Port Angeles፣ Raymond፣ Shelton፣ Tumwater፣ Vancouver |
መሰረታዊ ስልጠና 30 ለወላጅ ግለሰብ አቅራቢ፣ ውስን አገልግሎትና ለአዋቂ የህጻናት ተንከባካቢዎች ስልጠና ያስፈልጋል። ሁሉም 30 ሰዓቶች በኦንላይን ይጠናቀቃሉ።
መሰረታዊ ስልጠና 30ን መጀመር ከፈለጉ፣ ለመመዝገብ የሚረዱ መመሪያዎችን የያዘ ኢሜይል ይደርስዎታል።
ከ2/15/22 በፊት አንዳንድ መሰረታዊ ስልጠናዎችን 30 ካጠናቀቁ፣ ሆኖም ግን አሁንም የተወሰኑ ሞጁሎች ካሉዎት፣ ስልጠናዎን እንዴት እንደሚያጠናቅቁ መመሪያ የያዘ ኢሜይል ይላክልዎታል።
መሰረታዊ ስልጠና 7 ለወላጅ የግለሰብ አቅራቢ (DDA) የ 7-ሰዓት የሚያስፈልገው ስልጠና ነው።
ያሉትን ኮርሶች የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ቀኖች ለማየት በአካባቢዎቹ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
አካባቢ | ከተሞች |
---|---|
ምስራቃዊ ዋሽንግተን | Richland፣ Spokane |
Puget Sound | Bellingham፣ Everett፣ Kent፣ Lakewood፣ Seattle |
ማዕከላዊ ዋሽንግተን | በዚህ አካባቢ ምንም ወቅታዊ ትምህርቶች የሉም። |
ደቡብ ምዕራብ ዋሽንግተን | Bremerton፣ Vancouver |
ዌቢናሮች | የቀጥታ፣ አስተማሪ-መር የኦንላይን ክፍሎች። |
የተጨማሪ ትምህርት (CE) ኮርሶች ሙያዊ ችሎታዎትን ለማሳደግ እና ከደንበኞች ፍላጎት ጋር በጣም ተዛማጅ የሆኑ ርዕሶችን ለማሰስ እድል ይሰጡዎታል።
አሁን በአዲስ CEs መመዝገብ ይችላሉ። ኮርሶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ: