ተጨማሪ ትምህርት
ሁሉም የ CE መስፈርት ያላቸው ተንከባካቢዎች አሁን ወደ የእኔ ጥቅሞች (My Benefits) ገብተው ወደ የተንከባካቢ ትምህርት ማእከል በኦንላይን CEs፣ በአካል ክፍሎች ወይም ዌብናሮች መመዝገብ ይችላሉ። በCEs ውስጥ እንዴት እንደሚገቡና እንደሚመዘገቡ ይወቁ።
በእርስዎ ተመራጭ ቋንቋ CEን መውሰድ ከፈለጉ፣ ስላሉት የ CE አማራጮች ወይም እንዴት አስተርጓሚ መጠየቅ እንደሚችሉ የበለጠ ይወቁ።
Ver en español | 查看中文 | 한국어로 보기 | Посмотреть на русском | Xem bằng tiếng việt | عربى | Soomaali
ተጨማሪ የትምህርት ኮርሶች አሁን ይገኛሉ
የተጨማሪ ትምህርት (CE) ኮርሶች ሙያዊ ችሎታዎትን ለማሳደግ እና ከደንበኞች ፍላጎት ጋር በጣም ተዛማጅ የሆኑ ርዕሶችን ለማሰስ እድል ይሰጡዎታል።
አሁን በአዲስ CEs መመዝገብ ይችላሉ። ኮርሶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ:
የ CE ዝማኔ
ለ2019፣ 2020፣ 2021 ወይም 2022 የላቀ የCE መስፈርት ያሟሉ ሁሉም ተንከባካቢዎች በኦገስት 31፣ 2023 ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ቀን በኋላ፣ አመታዊ CE የማብቂ ቀንዎ የልደት ቀንዎ ነው።
አስፈላጊውን ስልጠና በቀነ-ገደብዎ ካልጨረሱ፣ እንደ ተከፋይ ተንከባካቢ መስራትዎን መቀጠል አይችሉም።
በጃንዋሪ 1 እና በኦገስት 31፣ 2023 መካከል የልደት ቀን ካለዎት፣ የእርስዎን 2023 CE ለማጠናቀቅ እስከ ኦገስት 31፣ 2023 ድረስ ጊዜ አለዎት።