Caregiver Kicks
ለተንከባካቢዎች ነፃ ጫማዎች
“የምን ጊዜም ምርጥ ጥቅም! ለማዘዝ በጣም ቀላል ነበር። የተለያዩ ስታይሎች ነበሩዎት። አግኝቼያቸዋለሁ እና ለብሼያቸዋለሁ። በጣም ተደስቼ ነበር ምክንያቱም በጣም ምቹ ናቸው።“
– John R.፣ ተንከባካቢ
ስለ Caregiver Kicks
የእርስዎን ነፃ* Caregiver Kicks — ማዳለጥን የሚከለካሉ ጫማዎችን — በየዓመቱ ያግኙ! Caregiver Kicks፦
- ምቹ ናቸው።
- በስራው ላይ ደህንነትዎን ይጠብቃሉ።
- እንደ Reebok እና Skechers ከመሳሰሉ ታዋቂ ስም ያላቸው ምርቶች የመጡ ሲታዩ በሚያምሩ እና ከ70 በላይ በሆኑ ስታይሎች ይገኛሉ።
ክሎጎች፣ ስኒከሮች፣ ከፍተኛ-ያለ ሆነ ጠፍጣፋ ታኮ ያላቸው፣ Caregiver Kicks ስራው የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ እንዲሆን የሚያስፈልጉዎት ጫማዎች ናቸው።
የደህንነት መረጃ ለCaregiver Kicks
Caregiver Kicks የእግር እና የጀርባ ህመምን እንደሚያሻሽል እና የሚያዳልጡ የቤት ውስጥ ወለሎችን ለመከላከል እንደሚረዳ ተንከባካቢዎች ይናገራሉ።
Caregiver Kicks ከመደበኛ ጫማዎች እንዴት እንደሚለዩ የበለጠ ለማወቅ “የደህንነት ምክሮች ለCaregiver Kicks”ን ይመልከቱ።
የእርስዎን Caregiver Kicks እርጥብ ወይም የሚያዳልጥ አካባቢ ላይ እንዳይንሸራተቱ በማገዝ በስራ ቦታዎ ላይ ደህንነትዎን ለመጠበቅ የተዘጋጁ ናቸው በበረዶ፣ በበረዷማ ሁኔታዎች ወይም በጂም ውስጥ ለመጠቀም የተዘጋጁ አይደሉም።
“እነዚህ ጫማዎች በእያንዳንዱ ተንከባካቢ መለበስ አለባቸው።”
– Brittany W.፣ ተንከባካቢ