መሰረታዊ ስልጠና 30
ሁሉንም የ 30 ሰዓታት ስልጠና በኦንላይን ማጠናቀቅ ይችላሉ። እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ይወቁ እና ስልጠናዎን ከዚህ በታች ያጠናቅቁ።
በ 8/17/2019 እና 9/30/2020 መካከል የተቀጠሩ እና መሰረታዊ ስልጠናን 30 ማጠናቀቅ የሚያስፈልጋቸው ተንከባካቢዎች የሚወስዱት የሰዓት ብዛት እና የቀነ-ገደብ መረጃ የያዘ ኢሜይል ሊደርሳቸው ይገባ ነበር። ይህንን ኢሜይል ካላዩ እና ስልጠናዎን ማጠናቀቅ ከፈለጉ፣ እባክዎ ለአባል የመርጃ ማዕከል (MRC) በ 1-866-371-3200 ይደውሉ ወይም በ mrc@myseiubenefits.org ኢሜይል ይላኩ። እነሱ ከሰኞ እስከ አርብ ከ 8 a.m. እስከ 4:30 p.m. ይገኛሉ።
የስልጠናዎ ቀነ-ገደቦች
በኮቪድ-19 ተጽእኖዎች የተነሳ የዋሽንግተን ስቴት ለተንከባካቢ ስልጠና መስፈርቶች ቀነ-ገደቡን አራዘመ። የማህበራዊ እና የጤና አገልግሎቶች መምሪያ (DSHS) በተቀጠሩበት ቀን መሰረት አዲስ ቀነ-ገደብ አዘጋጅቷል።
አስፈላጊውን ስልጠና በቀነ-ገደብዎ ካልጨረሱ፣ እንደ ተከፋይ ተንከባካቢ መስራትዎን መቀጠል አይችሉም።
የተቀጠሩበት ወይም ዳግም የተቀጠረቡት ቀን | መሰረታዊ ስልጠና መጠናቀቅ ያለበት በ |
ከ 8/17/2019 እስከ 9/30/2020 | 10/31/2022 |
ከ 10/1/2020 እስከ 4/30/2021 | 1/31/2023 |
ከ 5/1/2021 እስከ 3/31/2022 | 4/30/2023 |
4/1/2022 እስከ 9/30/2022 | 8/31/2023 |
የኦንላይን መለያዎን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ
- ወደ myseiu.be/online22 ይሂዱ። መለያ መፍጠር አያስፈልግዎትም።
- ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገቡ የሚከተለውን መረጃ ይጠቀሙ፦
- ለኢሜይልዎ፣ ሲቀጠሩ የሰጡትን የኢሜይል አድራሻ ይጠቀሙ።
- ለይለፍ ቃል፣ Summer2022 ይተይቡ።
- ልክ እንደገቡ የይለፍ ቃልዎን ያዘምኑ እና የእውቂያ መረጃዎን ያረጋግጡ።
- የኦንላይን ስልጠና ለመጀመር “ጀምር” ን ይጫኑ።
እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ፣ ለዝርዝር መመሪያዎች የመሰረታዊ ስልጠና 30 መመሪያን ይመልከቱ።[/vc_column_text][/vc_tta_section][vc_tta_section title=”ስልጠናዎን ማጠናቀቅ” tab_id=”Learn-More”][vc_row_inner][vc_column_inner][vc_column_text]መሰረታዊ ስልጠና 30 በራስ-ፍጥነት፣ በኦንላይን ላይ ብቻ የሚሰጥ የ 30 ሰዓታት ኮርስ ነው። ይህ የሚከተሉትን ያካትታ፦
- ለትምህርቱ የኦንላይን መግቢያ።
- በእያንዳንዱ ሞጁል መጨረሻ ላይ የዕውቀት ፍተሻ ያላቸው 11 የመማሪያ ሞጁሎች።
- የመጨረሻ ፈተና።
ከፌብሩዋሪ 22፣ 2022 በፊት ስልጠና ከጀመሩ፣ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉዎትን ኮርሶች በዳሽቦርድዎ ላይ ያያሉ። በአጠቃላይ፣ መሰረታዊ ስልጠና 30ን ለማጠናቀቅ የሚከተሉትን መውሰድ ያስፈልግዎታል።
- 5 ዋና ኮርሶች።
- የ 13 ሰዓታት ምርጫ ኮርሶች።
ይህ ኮርስ በአሁኑ ጊዜ የሚሰጠው በእንግሊዝኛ ብቻ ነው። በሌላ ቋንቋ ለመውሰድ እገዛ ከፈለጉ፣ የማህበረሰብ አስተርጓሚ መጠቀም ይችላሉ።
የማህበረሰብ አስተርጓሚ ማለት ደንበኛዎ ያልሆነ እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ጓደኛ ወይም ዘመድ ነው።
[/vc_column_text][/vc_tta_section][vc_tta_section title=”ጥያቄዎች አሉዎት?” tab_id=”Questions”][vc_column_text]ጥያቄዎች አሉዎት?
ስልጠናዎን ለመመዝገብ እና ለማጠናቀቅ እርዳታ ከፈለጉ፣ የመሰረታዊ ስልጠና 30 መመሪያን ይመልከቱ።
ለተጨማሪ ድጋፍ፣ የአባል መርጃ ማዕከልን (MRC) ያነጋግሩ።
- ስልክ ቁጥር፦ 1-866-371-3200፣ ከሰኞ–ዓርብ፣ 8 a.m.–4:30 p.m.
- ኢሜይል: mrc@myseiubenefits.org
- የመጀመሪያ ቋንቋዎ እንግሊዘኛ ካልሆነ፣ በMRC ውስጥ ያሉ ተወካዮች በቋንቋዎ ከእርስዎ ጋር ሊነጋገሩ ይችላሉ።