የአሰሪ ምዝገባ ለውጥ

Ver en español | 查看中文 | 한국어로 보기 | Посмотреть на русском | Xem bằng tiếng Việt | عربى | Soomaali

የአሰሪ ምዝገባ ለውጥ

እርስዎ በሸማች ቀጥታ እንክብካቤ ኔትወርክ ዋሽንግተን (Consumer Direct Care Network Washington) ወይም CDWA ወደ ተቀጣሪነት ስለሚሸጋገሩ የአሰሪዎን ለውጥ ተከትሎ ለጤና እንክብካቤ ሽፋን (እንደ ክፍት ምዝገባ) ተመሳሳይነት የምዝገባ ጊዜ ይኖራል። 

የመመዝገቢያ ጊዜው “የአሰሪ ምዝገባ ለውጥ” (COEE) ይባላል እና በምዝገባው ወቅት የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ:

 • “በ SEIU 775 Benefits Group (ብቁ ከሆኑ) በኩል ለጤና ሽፋን ያመልክቱ።
 • “የጥርስ ህክምና እቅድ (ተመዝግበው ከሆነ) ላይ አማራጭ ለውጦችን ማድረግ።
 • በፕሪሚየም ሙሉ ወጪ ጥገኛን* ያክሉ። 

ስለ የአሰሪ ምዝገባ (COEE) ለውጥ ማወቅ ያለብዎት ነገር: 

 • የመመዝገቢያ ጊዜዎ በ CDWA የሽግግር ቀንዎ ይወሰናል። 
 • ከሴፕቴምበር 1፣ 2021** ጀምሮ ወደ CDWA DirectMyCare የድር መግቢያ በር ይግቡ እናም ሁሉንም የ CDWA የቅጥር ስራዎችዎን ያጠናቅቁ።
  • ይህ በ CDWA ተቀጥረው ለመቀጠር እየተሸጋገሩ መሆኑን በ DSHS ወይም በ CDWA ለተነገራቸው ተንከባካቢዎች ብቻ የሚውል ነው። 
  • በጤና ሽፋንዎ ውስጥ መቋረጥ አለመኖሩን ለማረጋገጥ (ወይም ለማመልከት፣ ብቁ ከሆኑ) በተቻለ ፍጥነት ስራዎችዎን ያጠናቅቁ።
 • አንዴ የ CDWA ሽግግርዎን ከጨረሱ በኋላ የአሰሪ ምዝገባ ጥቅል ለውጥ በፖስታ ይቀበላሉ። 
 • ሽፋን ውስጥ ለመመዝገብ (ብቁ ከሆኑ እና ማመልከቻ ካስገቡ) ወይም አማራጭ ለውጦችን (አስቀድመው ከተመዘገቡ) ለማድረግ የእርስዎ ጥቅል የ 60-ቀን ምዝገባ መስኮትዎን ያሳውቅዎታል። 
  • አስቀድመው በጤና ጥቅሞች ውስጥ ተመዝግበው ከሆነ፣ ለውጦችን ማድረግ ካልፈለጉ በስተቀር ማመልከቻ መሙላት አያስፈልግዎትም።
 • በ CDWA ወደ ተቀጣሪነት በሚሸጋገሩበት ጊዜ ሰዓቶችዎን በወቅቱ ማሳወቅዎን ያረጋግጡ።

 

የሚያገኙት ነገር

ለ $25 በወር፣ የሚከተሉትን የጤና እንክብካቤ ጥቅሞች ያገኛሉ፡

 • ሜዲካል
 • ነፃ ተቀዳሚ እንክብካቤ ጉብኝቶች
 • የጥርስ ሕክምና
 • ኦርቶዶንቲያ
 • የማየት ችሎታ
 • መስማት ችሎታ
 • መውለድ መቻል
 • በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት
 • የስሜት ድጋፍ

 

ከከፍተኛ ጥራት የጤና እና የጥርስ ህክምና እቅዶች በተጨማሪ፣ ለእርስዎ ብቻ ተብለው የተዘጋጁ የጤና እና ደህንነቱን የጠበቀ ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት ይችላሉ:

 • የራስ እንክብካቤ ማድረገግ ጥቅሞች: የስነ ልቦና ጤና ፕሮግራሞች ጭንቀት፣ ድብርት እና ስጋትን ለመቀነስ ይረዳሉ። ፍላጎትዎን የሚያሟላ ራስን የመንከባከብ እርዳታ ያግኙ። 
 • የእንክብካቤ ሰጪ ጫማዎች: ነጻ፣ ምቹ እና የማያንሸራትቱ ጫማዎችን ከ70 ስታይሎች ያግኙ። ስለ እንክብካቤ ሰጪ ጫማዎች የበለጠ ይወቁ

 

እንዴት መመዝገብ ወይም ለውጦችን ማድረግ እንደሚቻል

ብቁ ከሆኑ ወይም ከተመዘገቡ፣ ሽፋን ለማግኘት ማመልከት ወይም የወረቀት የጤና ጥቅሞችን ማመልከቻ በፋክስ ወይም በደብዳቤ ማስገባት ይችላሉ። 

ወደ CDWA ሽግግርዎን ከጨረሱ በኋላ ለመሙላት እና በፖስታ ለመላክ በወረቀት የጤና ጥቅሞች ማመልከቻ በፖስታ ውስጥ ጥቅል ይቀበላሉ። ፖስታ መላክ አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን የምዝገባ ቅጾን መመለስ ቀላል ነው። 

ደብዳቤ ፋክስ
SEIU 775 Benefits Group
ፖስታ ሳጥን 24811
Seattle, WA 98124
 

516-723-7395

የአሰሪ ምዝገባ ጥቅል (የጤና ጥቅሞችን ማመልከቻ) ካልቀበሉ እና ሊኖርዎት እንደሚገባ ብለው የሚያስቡ ከሆነ ወይም ማመልከቻዎን ባስገቡ በ 45 ቀናት ውስጥ ለመመዝገብ የማረጋገጫ ደብዳቤ ካልተቀበሉ ወይም በፖስታ ውስጥ ለውጦችን ለማቀድ እቅድ ካላገኙ ለ SEIU 775 ጥBenefits Group Customer Service በ 1-877-606-6705 ይደውሉ።

የበለጠ ዝርዝር

ብቁነት ለሽፋኑ ብቁ ለመሆን፣ ለ 2 ወራት በተከታታይ በየወሩ 80 ሰአታት መስራት እና ቀጣይ ለሆነ ሽፋን ደግሞ በወር 80 ሰአታት መስራትዎን መቀጠል አለባቸው።

የእቅድ ለውጦች እንደ አማራጭ ናቸው: ተመዝግበው ምንም የማየሰሩ ከሆነ፣ ለ CDWA መስራትዎን እስከቀጠሉ እና ሰዓቶችዎን እስካቀርቡ ድረስ ተመሳሳይ የሆነ የጤና ሽፋንዎ መቀበልዎን ይቀጥላሉ። 

ሽፋኑ መቼ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ: የጤና ጥቅሞች ማመልከቻዎ ኖቬምበር 15፣ 2021 ወይም ከዚያ በፊት ከተረከበ አዲሱ ሽፋንዎ ወይም የሽፋን ለውጦችዎ ከዲሴምበር 1፣ 2021 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ።

ማመልከቻዎ ከኖቬምበር 15፣ 2021 በኋላ ከተረከበ፣ አዲሱ ሽፋንዎ ወይም የሽፋን ለውጦችዎ ተግባራዊ ከሆኑበት ቀን ጋር ደብዳቤ ይላክልዎታል።

*አዲስ! በ CDWA ተቀጥረው ለሚሰሩ IPዎች – ጥገኞችን ማከል: በራስ-ሰር የደመወዝ ክፍያ ቅነሳ በኩል ሙሉውን ፕሪሚየም ከከፈሉ አሁን ጥገኛ የሆኑ ልጆችዎን በጤና እና ጥርስ ሽፋን ውስጥ መመዝገብ ይችላሉ። ሙሉ ፕሪሚየሞች በወር ከ $686-$766 ይደርሳሉ።

ጥገኛ(ኞች)ን ለማከል፣ የጤና ጥቅሞችን ማመልከቻ ጥገኛ ክፍል መሙላት እና ከዚያ በ 60 ቀናት ውስጥ ለጥገኛ(ኞችዎ) ማረጋገጫ ማቅረብ አለብዎት። ከዚያም በደመወዝ ቅነሳ በኩል ፕሪሚየሙን መክፈል ይጀምራሉ። ሽፋኑ ዲሴምበር 1 ወይም ከዚያ በኋላ ይጀምራል። ጥገኛን ስለማከል የበለጠ ይወቁ።

 

ጥያቄዎች አሉዎት?

በ 1-877-606-6705 ለጤና ጥበቃ ሽፋን ደንበኛ አገልግሎት ይደውሉ።