IPዎች: ወደ CDWA ሽግግርዎ

ምን እንደሚጠበቅ

Ver en español | 查看中文 | 한국어로 보기 | Посмотреть на русском | Xem bằng tiếng Việt | عربى | Soomaali

አሰሪዎ Department of Social and Health Services/ከማህበራዊ እና ጤና አገልግሎቶች መምሪያ (DSHS) ወደ Consumer Direct Care Network Washington/የሸማች ቀጥታ እንክብካቤ አውታረ መረብ ዋሽንግተን (CDWA) እየቀየረ ነው። ሽግግር ላይ መሆንዎን በ DSHS ወይም CDWA እንዲያውቁ የተደረጉ ተንከባካቢ ከሆኑ፣ ወደ CDWA DirectMyCare የድር መግቢያ በመግባት ሽግግርዎ በተቀላጠፈ ሁኔታ መከናወኑን ለማረጋገጥ ሁሉንም የቅጥር ስራዎችዎን ማጠናቀቅ ያስፈልግዎታል

ምን ማድረግ እንዳለብዎ እና በሽግግሩ ወቅት ጥቅማ ጥቅሞችዎ አስመልክቶ ምን እንደሚጠብቁ ከዚህ በታች መረጃ ያገኛሉ።

ተጨማሪ ይወቁ:

 

ወደ CDWA ሽግግር ለማድረግ ምን ማድረግ የሚጠበቅብዎት

ወደ አዲሱ አስሪዎ የተሳለጠ ሽግግር ማድረግዎን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት:

  • ወደ CDWA DirectMyCare ድር መግቢያ መግባት እና ሁሉንም የቅጥር ስራዎችዎን ማጠናቀቅ ያስፈልግዎታል። ከ InfoCDWA@ConsumerDirectCare.com የደረጃ በደረጃ መመሪያዎችን ጨምሮ የይለፍ ቃል (ቀደም ሲል በእርስዎ የተፈጠረ መለያ) ለመቀየር መጠቀም ያለብዎትን ማስፈንጠሪያ የያዘ ኢሜይል ይቀበላሉ።
  • ስለ CDWA እና የሽግግሩ ሂደት ዝማኔዎችን ለማግኘት በየጊዜው ኢሜይልዎን ይፈትሹ። ኢሜይል እንዳያመልጥዎት ለመፈተሽ የአይፈለጌ መልእክት ወይም አላስፈላጊ አቃፊዎችዎን ይፈትሹ።

እንደ CDWA ሰራተኛ "እንክብካቤ ማቅረብ እንደሚችሉ" ከ CDWA ማረጋገጫ እስኪያገኙ ድረስ ሽግግርዎ አልተጠናቀቀም። በሽግግር ሂደትዎ ላይ እገዛ ከፈለጉ፣ በ 866-214-9899 ይደውሉ፣ ለ InfoCDWA@ConsumerDirectCare.com ኢሜይል ያድርጉ ወይም www.ConsumerDirectWA.comን ይጎብኙ።

 

በዚህ ሽግግር ወቅት ስለ ጥቅማጥቅሞዎ ምን እንደሚጠብቁ

ትምህርት

ወደ ሲዲኤኤ CDWA፣ ስልጠናዎ በስልጠና መርሃ ግብርዎ ላይ ሳይቋረጥ ወይም በመስፈርቶችዎ ላይ ለውጦች ሳይኖር ይቀጥላል። መሰረታዊ የስልጠና መስፈርት ያላቸው አዲስ ተንከባካቢ ቢሆኑም ወይም ቀጣይ ትምህርትን መውሰድ ቢያስፈልግዎት ይህ እርግጥ ነው። በስልጠናዎ ወቅት ለደንበኛዎ (ወይም ለተፈቀደለት ወካይ) ሽፋን ለማመቻት፣ አሁንም ከአሰሪዎ (አሁን CDWA) ጋር መስራት ይኖርብዎታል። 

በኢሜይል የገቢ መልዕክት ሳጥንዎ ውስጥ ስለአስፈላጊ ስልጠናዎ ማሳወቂያዎችን መፈለግዎን ይቀጥሉ። ኢሜይል እንዳያመልጥዎት ለመፈተሽ የአይፈለጌ መልእክት ወይም አላስፈላጊ አቃፊዎችዎን ይፈትሹ።

ስለ ትምህርት ጥቅሞችዎ የበለጠ ይወቁ።

ጤና

በ SEIU 775 Benefits Group በኩል የጤና እንክብካቤ ሽፋን ካለዎት እንዲሁም ለሽፋን ብቁ ሆነው ከቀጠሉ፣ ሽፋንዎ ያለማቋረጥ ይቀጥላል። እርስዎ ብቁ ከሆኑ እና ለጤና እንክብካቤ ሽፋን ማመልከት ወይም አሁን ባለው ሽፋንዎ ላይ አማራጭ ለውጦችን ማድረግ ከፈለጉ፣ ከአመታዊ ክፍት ምዝገባ ጋር የሚመሳሰል ልዩ የጊዜ (በየአመቱ በጁላይ ይከሰታል) ይኖራል። 

ይህ የመመዝገቢያ ጊዜ የአሰሪ ምዝገባ ለውጥ (COEE) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የሚከናወነው በ CDWA ለመቀጠር ስለሚሸጋገሩ ነው። ስለ COEE ተጨማሪ መረጃን በፖስታ እና ኢሜይል ያገኛሉ።

ሽፋን ለማግኘት (ብቁ ከሆኑ እና የሚያመለክቱ ከሆነ) ወይም በእርስዎ ሽፋን ላይ አማራጭ ለውጦችን ለማድረግ፣ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት:

✓ የ CDWA ሽግግርዎን (በ DirectMyCare ድርመግቢያ በኩል) በወቅቱ ያጠናቅቁ።

✓ ሰዓቶችዎን በወቅቱ ሪፖርት ያድርጉ።

✓ የጤና የጥቅማ ጥቅም ማመልከቻል ይሙሉ እና ያስገቡ (የሚያመለክቱ ወይም ለውጦችን የሚያደርጉ ከሆነ)።

ስለ አሰሪ ምዝገባ ለውጥ ተጨማሪ ይወቁ።

ጡረታ

የ SEIU 775 ደህንነቱ የተጠበቀ የጡረታ እቅድ ለተንከባካቢዎች ልማድ የመጀመሪያው ነው። ተንከባካቢዎች የ 6 ወር ተሳትፎ መስፈርቱን ካሟሉ በኋላ በራስ-ሰር በእቅዱ ውስጥ ተመዝግበዋል። ጡረታ ሲወጡ ወይም የጡረታ ዕድሜ ላይ ሲደርሱ የጡረታ ድጎማ መቀበልን መጀመር ይችላሉ። 

ከ DSHS/IPOne ወደ CDWA መሸጋገር የወደፊት ሰዓቶችዎን ወይም ለጡረታዎ በሚሰጡ መዋጮዎች ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም። ወደ CDWA ከተሸጋገሩ በኋላ ተመሳሳይ የጡረታ ጥቅማ ጥቅሞችን ያገኛሉ።

የኦንላይን ጡረታ My Plan መለያ ከሌለዎት፣ ዛሬ አንድ ይፍጠሩ! ሂሳብዎን ማየት እና የእውቂያ መረጃዎን እና ተጠቃሚዎችን ማዘመን ይችላሉ። 

ስለ ጡረታዎ ጥቅሞችዎ የበለጠ ይወቁ።

ስራ-ማዛመድ 

ወደ CDWA ከተሸጋገሩ በኋላ አሁንም በ Carina በኩል የስራ-ማዛመድ ጥቅሞችን ያገኛሉ። Carina ተጨማሪ ሰዓቶች ከፈለጉ ሊጠቀሙባቸው ከሚችሏቸው ደንበኞች ጋር ተንከባካቢዎችን የሚዛምድ ድረገፅ ነው። Carina በአካባቢዎ ውስጥ የመጠባበቂያ እንክብካቤን እንዲያገኙም ይረዳዎታል። 

ስለ Carina የበለጠ ይወቁ። 

 

ስለ CDWA ተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች

ስለ CDWA በተደጋጋሚ ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልሶችን ይመልከቱ።

 

ጥያቄዎች አሉዎት?

ወደ CDWA ሽግግር በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች ወይም የወረቀት ስራዎን ለመሙላት እርዳታ ከፈለጉ፣ ወደ 866-214-9899 ይደውሉ፣ ለ InfoCDWA@ConsumerDirectCare.com ኢሜይል ይላኩ ወይም www.ConsumerDirectWA.comን ይጎብኙ።

ስለ ቀጣሪ ምዝገባ ለውጥ ጥያቄዎች፣ በ 1-877-606-6705 ለ SEIU 775 የጥቅማ ጥቅሞች ቡድን የደንበኛ አገልግሎት ይደውሉ።

በሽግግሩ ወቅት ስለ ጥቅማ ጥቅሞችዎ ጥያቄዎች፣ በ 1-877-371-3200 ለአባል ግብዓት ማዕከል (MRC) ይደውሉ።