ብቃቱ የተረጋገጠ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ (HCA) መሆን

የምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚተገበሩ እርምጃዎች

እንደ ተንከባካቢ ስራዎን ስለጀመሩ እንኳን ደስ አለዎት!

ስልጠናዎን ከመጀመርዎ በፊት ወይም እንደ ተከፋይ ተንከባካቢ ከመስራትዎ በፊት፣ ገላፃ እና ደህንነት (O&S) ማጠናቀቅ ያስፈልግዎታል።

O&S ን እንዴት ማጠናቀቅ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ይማሩ። 

 

 

የ DOH የምስክር ወረቀት ማመልከቻ ያስገቡ — ከ 1–14 ቀናት

እንደ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ሰጪ ለመሆን፣ በተቀጠሩ በ 14 ቀናት ውስጥ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ሰጪ (HCA) የምስክር ወረቀት ማመልከቻ (እንዲሁም “DOH ማመልከቻ” ተብሎ የሚጠራው) ማጠናቀቅ አለብዎት። ይህ ማመልከቻ ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት ሊረከብ ይችላል።

የማመልከቻውን ክፍያ መክፈል አይጠበቅብዎትም። በ SEIU 775 እንደ የእርስዎ ጥቅሞች ማመልከቻ እና የመጀመሪያ ጊዜ የፈተና ክፍያዎች ተሸፍነዋል።

የእንግሊዝኛ ችሎታዎ የተገደበ ከሆነ፣ የምስክር ወረቀት ያለው HCA ለመሆን እስከ 60 ተጨማሪ ቀናት ሊፈቀድልዎ ይችላል። ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ለማመልከት፣ በHCA ማረጋገጫ ማመልከቻ ገፅ 1 ላይ “ለጊዜያዊ የምስክር ወረቀት እያመለከትኩኝ ነው” በሚለው ሳጥን ላይ ምልክት ማድረግ አለብዎት።

ማመልከቻዎን በኦንላይን ወይም በፖስታ ማስገባት ይችላሉ።

ኦንላይን

ይህን የ 3-ደቂቃ ዩቲውብ ቪዲዮ ከጤና መምሪያ (DOH) ይመልከቱ። በመለያ በመግባት፣ ማንነትዎን በማረጋገጥና ማመልከቻውን በኦንላይን በመሙላት ይመራዎታል። በኦንላይን ከማመልከትዎ በፊት ማወቅ ያለብዎት ነገሮች፡-
  • “የስቴት ክፍያ” ን ማረጋገጥዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
  • የኦንላይን የማመልከቻ ጥያቄዎች ወደ DOH በኢሜይል በ hmccreview@doh.wa.gov ወይም በስልክ 360-236-2700 ማስገባት ይችላሉ።
  • ከDOH ምንም ኢሜይሎች እንዳላመለጥዎት ለማረጋገጥ የአይፈለጌ መልዕክት ማህደርዎን ይመልከቱ።

ደብዳቤ

ደረጃ 1 – የ DOH ማመልከቻዎን ይሙሉ (ማስታወሻ፡ ምንም ክፍያ አያስፈልግም)።
ደረጃ 2 የረጅም ጊዜ እንክብካቤ የቅጥር ማረጋገጫ ቅፁን ይሙሉ።

ወደሚከተለው ይላኩላቸው፡
Department of Health
Home Care Aide Credentialing
PO Box 1099
Olympia, WA 98507-1099

በመሰረታዊ ስልጠና ይመዝገቡ

የግለሰብ አቅራቢዎች

የመሰረታዊ የስልጠና ፍላጎትዎን በመጨረሻው ቀን ማጠናቀቅ ያስፈልግዎታል። በመሰረታዊ ስልጠና ስለመመዝገብና የስልጠና መስፈርቶትን ስለማሟላት የሚገልፅ መረጃ የያዘ ኢሜይል ወይም የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል።

የኤጀንሲ አገልግሎት አቅራቢዎች 

ለመመዝገብ በጣም ጥሩውን መንገድ ከቀጣሪዎ ጋር ይፍትሹ።

የተሟላ መሰረታዊ ስልጠና — ቀናት 30-60

በአካባቢዎ ያሉትን ክፍሎች እና የሚመርጡትን ቋንቋ በተሻለ መንገድ ማግኘት እንዲችሉ በተቻለ ፍጥነት ስልጠናዎን ይውሰዱ።

ለፈተናዎ ይዘጋጁ — ከ 60-90 ቀናት

መሰረታዊ ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላ ፕሮሜትሪክ የፈተና ቀንዎን በኢሜይል ይልካል። ኢሜይል ካልደረስዎ፣ የቆሻሻ መጣያ እና አይፈለጌ መልዕክት ማህደሮችን ይመልከቱ ወይም Prometric ን በ 1-800-324-4689 ያነጋግሩ።

እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል፡-

  • በ 13 ቋንቋዎች የሚገኘውን የፕሮሜትሪክ ፈተና መሰናዶ ማቴሪያሎችን ይገምግሙ።
  • Peer Mentor (የአቻ ለአቻ አሠልጣኝ) ጋር ይገናኙ።
    • Peer Mentors (የአቻ ለአቻ አሠልጣኞች) እንደ እርስዎ ያሉ አዲስ ተንከባካቢዎችን የሚያግዙ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ሰጪዎች የተመሰከረላቸው ናቸው። ስለሚያቀርቡት የነፃ የማስተማሪያ ግብዓቶች የበለጠ ለማወቅ የ Peer Mentor (የአቻ ለአቻ አሠልጣኝ) ገፅን ይጎብኙ።
  • ነፃ* ማደሻ ኮርስ ያውጡ።
    • ይህ የ 2 ሰአት በአካል መገኘት ኮርስ በፕሮሜትሪክ የመረጣችሁትን ማንኛውንም የተግባር ችሎታዎች በመማሪያ ክፍል ውስጥ እንዲለማመዱ በማድረግ ለማረጋገጫ ፈተና ያዘጋጅዎታል። Peer Mentors (የአቻ ለአቻ አሠልጣኞች) የማደሻ ኮርስ መርሀግብር ሊያግዙ ይችላሉ። በ 855-803-2095 ይደውሉላቸው ወይም በ peer.mentorship@myseiubenefits.org ኢሜይል ይላኩላቸው።
*የማደሻ ኮርሶች አያስፈልጉም እና ለመታደም ክፍያ አያገኙም።

ፈተና ይውሰዱ — ቀናት 90-120

በፈተናዎ ቀን፡-

  • ከታቀደልዎት ፈተና ቢያንስ 30 ደቂቃ በፊት ይድረሱ። ዘግይተው የሚመጡ ሰዎች ፈተናውን እንዲወስዱ አይፈቀድላቸውም እናም ለተጨማሪ ቀጠሮ ቀን የፈተና ክፍያ መክፈል አለባቸው።
  • የእርስዎን “የፈተና መግቢያ” (ATT) ደብዳቤ እና 2 ትክክለኛ የመታወቂያ ቅፆችን ይዘው ይምጡ።

የእውቅና ማረጋገጫዎን ማስጠበቅ

ውጤቶችዎ ለ DOH ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን እርስዎ በይፋ ማረጋገጫ እንዳገኙ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ይልክልዎታል።

የምስክር ወረቀት ያለዎት HCA ከሆኑ በኋላ፣ አብዛኛውን ጊዜ የልደትዎ የሆነበት የእያንዳንዱ አመት በስልጠና ቀነ-ገደብዎ የ 12 ሰአታት ተከታታይ ትምህርት (CE) ማጠናቀቅ አለብዎት። ቀኑን ለማረጋገጥ ወደ ተንከባካቢ የመማሪያ ማዕከል ይሂዱ።


በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

በተቀጠሩ በ 14 ቀናት ውስጥ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ሰጪ ማረጋገጫ ማመልከቻን ለጤና መምሪያ (DOH) ማስገባት አለብዎት።

ስልጠናው ካበቃበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የፈተና ቀን ማሳወቂያ ካልደረሰዎት፣ ፕሮሜትሪክን በ 1-800-324-4689 ማግኘት አለብዎት።

 

አይ። ከሜይ 1፣ 2016 በፊት፣ ለ DOH ማረጋገጫ እና እንዲሁም ለፈተና ፕሮሜትሪክ ማመልከቻ መሙላት ያስፈልግዎታል። ሆኖም ግን ከሜይ 1 ቀን 2016 ጀምሮ እነዚያ ማመልከቻዎች ተጣምረዋል።

የተጠናቀቁ ማመልከቻዎች አሁን ለ DOH ተረክበዋል። ፕሮሜትሪክ ፈተናውን መስጠት ይቀጥላል። አንድ አመልካች ሁሉንም መስፈርቶች ካሟላ በኋላ፣ DOH ፈተናውን የጊዜ ሰሌዳ እንዲያዝለት ለፕሮሜትሪክ ያሳውቃል።

ፕሮሜትሪክ ያለ ኢሜይል አድራሻ የማረጋገጫ ፈተና ቀጠሮ እንደማይሰጥ ልብ ይበሉ። ከ DOH እና/ወይም ከፕሮሜትሪክ ለሚመጣ ግንኙነት አመልካቾች አላስፈላጊና አይፈለጌ መልዕክት ማህደሮችን ጨምሮ ኢሜይላቸውን በመደበኛነት መፈተሽ አለባቸው። የኢሜይል አድራሻ የሌላቸው አመልካቾች ኢሜላቸውን በተደጋጋሚ የሚፈትሽ እና መረጃ የሚያደርስውን ግለሰብ የኢሜይል አድራሻውን መዘርዘር አለባቸው።

ማንኛቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት፣ በ (360) 236-2700 የጤና ጥበቃ መምሪያን ያግኙ።