በአካል እና በዌቢናር CE ኮርሶች

አሁን በተጨማሪ ትምህርት (CE) ዌቢናር እና በአካል ኮርሶች መመዝገብ ይችላሉ።

የሚገኙ የ CE ኮርሶች፡

ከዚህ ቀደም ለጨረሱት የ CE ኮርስ ክሬዲት ማግኘት ስለማይችሉ እባክዎ ከዚህ ቀደም ላልወሰዷቸው ኮርሶች ይመዝገቡ።

የ CE ኮርሶች በብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ። የአባል የግብዓት ማዕከል (MRC) የቋንቋ ተገኝነትን መፈተሽ ይችላል።

ስለ CE ቀነ-ገደቦች ጠቃሚ መረጃ

የ CE ቀነ-ገደቦች የኮቪድ-19 የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ካበቃ በኋላ እስከ 120 ቀናት ድረስ ተራዝመዋል፣ ይህም በአሁኑ ጊዜ ኤፕሪል 16፣ 2022 ያበቃል። ይህ ማለት የ CE ቀነ-ገደብ ኦገስት 14፣ 2022 ነው።

CEs ለማጠናቀቅ እየጣሩ ሳሉ፣ እንደ ተከፋይ ተንከባካቢ መስራትዎን እና ክፍያ ማግኘት መቀጠል ይችላሉ።

እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል

የግለሰብ አቅራቢዎች (Ips) ለአባላት ግብዓት ማዕከል (MRC) በ 1 (866) 371-3200 ከሰኞ – አርብ ከ 8 a.m. እስከ 4፡30 p.m. የፓሲፊክ ሰዓት በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።

የኤጀንሲ አገልግሎት አቅራቢዎች (APs) አሰሪያቸውን በማነጋገር መመዝገብ ይችላሉ።

 

CE ኮርሶች

ጥንቃቄ የተሞላበት አመጋገብ

  • CE ክሬዲት፡-
    • 2 ሰዓታት።
  • የኮርሱ ቅርፀት፡-
    • በዌቢናር እና በአካል።
  • የኮርሱ መግለጫ፡-
    • ስለ አዕምሮዓዊነት ፅንሰ-ሀሳብ እና ጥንቃቄ በመብላት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይማሩ። እርስዎ ረሃብን በጥቃቄ የተሞላ አመጋገብ ዓይን በመመልከት ይመረምራሉ እና ምርጥ ልማዶችን በጥንቃቄ የተሞላ አመጋገብ ውስጥ ተግባራዊ ያደርጋሉ።

የባይፖላር በሽታ ያለባቸውን ደንበኞች መንከባከብ

  • CE ክሬዲት፡-
    • 2 ሰዓታት።
  • የኮርሱ ቅርፀት፡-
    • በዌቢናር እና በአካል።
  • የኮርሱ መግለጫ፡-
    • እንዴት የባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር የበሽታ ምልክቶችን ሪፖርት ማድረግ እንደሚቻል፣ እንዴት ከተለመደው መሠረታዊ ባሕሪ ለውጦች ሲኖሩ እንዴት ሪፖርት እንደሚደረግ፣ እና ባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸውን ደንበኛ ለማገዝ እንዴት ትክክለኛ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚቻል ይማሩ። እርስዎ ራስን በራስ ማጥፋትን በመከላከል ላይ ለማገዝ እንዴት ተገቢነት ያላቸው እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይማራሉ እንዲሁም ከባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር ጋር ግንኙነት ያላቸው አጋዥ ግብዓቶች ይሰጡታል።

የእንክብካቤ ሰጪ ምርጥ አሠራሮች፦ ከልክ በላይ መጨናነቅ

  • CE ክሬዲት፡-
    • 2 ሰዓታት።
  • የኮርሱ ቅርፀት፡-
    • በአካል ብቻ።
  • የኮርሱ መግለጫ፡-
    • እንዴት ከልክ በላይ መጨናነቅን ማብራራት፣ ከልክ በላይ መጨናነቅን የመከላከል አስፈላጊነት በአጭር ማስቀመጥ፣ እና ከልክ በላይ የመጨናነቅ ምልክቶችን ለይቶ ማወቅ እንደሚቻል ይወቁ። እርስዎ ከልክ በላይ በመጨናነቅ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ እንደ አጋዥ መሣሪያዎችን የሚያካትቱ ሥራዎችን እንዴት መሥራት እንደሚቻል እና እንዴት ደንበኛን ወይም አንድ እቃ ደኅንነትን በጠበቀ መልኩ እንዴት ማንቀሳቀስ እንደሚቻል የመሳሰሉ ምርጥ አሠራሮችን ሞዴል ያደርጋሉ።

በቃል የማረጋጊያ ቴክኒኮች

  • CE ክሬዲት፡-
    • 6 ሰዓታት።
  • የኮርሱ ቅርፀት፡-
    • በአካል ብቻ።
  • የኮርሱ መግለጫ፡-
    • ስለ ተረበሸ ባሕሪ እና የተረበሸን ደንበኛ ጨምሮ በንዴት የጦዘን እንዴት በንግግር ማረጋጋት እንደሚቻል ይማሩ። በንዴት የጦዘን በንግግር ማረጋጋት ደንቦች እና ስሜቱ በተረበሸ ደንበኛ ላይ እንዴት ተፈጻሚ ሊደረጉ እንደሚችሉ፤ እንዴት LOWLINE ሞዴልን ከደንበኛው ጋር አንድ ነገር እየተወሳሰበና እየጦዘ ሲሄድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፤ ሦስት ዓይነት የተረበሸ ባሕሪን ለይቶ ማወቅ እና በአግባቡ እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል፤ እንዲሁም ከአስቸጋሪ ገጠመኝ በኋላ ራስን የመግለጽ ልምምዶችን የኮርሱ ርእሰ ጉዳዮች ያካትታሉ።

የጤና ድጋፍ ቡድን ስልጠና

  • CE ክሬዲት፡-
    • 3 ሰዓታት።
  • የኮርሱ ቅርፀት፡-
    • በዌቢናር ብቻ።
  • የኮርሱ መግለጫ፡-
    • ደንበኛዎን እና እራስዎን ከድህረ-አደጋ እንዲያገግሙ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ይማሩ። በአደጋ ባህሪ ጤና ስልጠና ቅርፀት ውስጥ የስነ-ልቦና እና ትምህርታዊ መረጃዎችን በማቅረብ የማገገም ችሎታን ለማዳበር ይረዳዎታል።

Students with Disabilities

Students with disabilities have the right to request and receive reasonable accommodation so they can take full advantage of the Training Partnership’s programs and activities. Learn more about our reasonable accommodation policy.

Learn More