አሁን እገዛ ያግኙ
ለስሜታዊ ደህንነትዎ ግብዓቶች
ነጻ እርዳታ አሁን | ነጻ እርዳታ በማንኛውም ጊዜ | ነፃ እርዳታ በSEIU 775 Benefits Group የጤና ጥቅማ ጥቅሞች
የግል ህይወት እገዛ ወይም የስሜታዊ ደህንነት ግብዓቶችን ከፈለጉ፣ አሁኑኑ ለእርስዎ በርካታ ነጻ አማራጮች አሉ።
አስታውሱ፣ ብቻዎን አይደሉም! ከሁሉም ተንከባካቢዎች ውስጥ እስከ ግማሽ ያህሉ ጭንቀት የሚያጋጥማቸው ሲሆን ከ 5 ተንከባካቢዎች ውስጥ 1 ተንከባካቢ ከመካከለኛ-እስከ-ከባድ የመንፈስ ጭንቀት ያጋጥማቸዋል። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በህይወታቸው ውስጥ በሆነ ወቅት በስሜታዊ ጤንነት ህክምና ሁኔታ ይታወቃሉ።
ለስሜታዊ ደህንነትዎ እንክብካቤ ማድረግ ልክ እንደ አካላዊ ጤንነትዎ ሁሉ አስፈላጊ ነው።[/vc_column_text][vc_column_text]
Get Help Now
ከሆነ ሰው ጋር ወዲያውኑ ያነጋግሩ እና እገዛ ያግኙ። እነዚህን አገልግሎቶች በየዕለቱ ለ 24 ሰዓታት በማንኛውም የሳምንቱ ቀን ለመደወል ነፃ ነው።
ከታች ያሉት ሁሉም አገልግሎቶች በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ እና ከ150 በላይ ቋንቋዎች በቋንቋ እርዳታ ይገኛሉ።[/vc_column_text][vc_column_text]
ስሜታዊ ጭንቀት | |
988፣ ለ ራስን ማጥፋት እና ቀውስ ላይፍላይን፣ ቀደም ሲል ብሄራዊ ራስን ማጥፋት መከላከል ላይፍላይን ተብሎ የሚታወቀው ይህ የስልክ መስመር በስሜታዊ ጭንቀት ውስጥ ላሉ ሰዎች ከሰለጠኑ አማካሪዎች ነፃና ሚስጥራዊ ድጋፍ ይሰጣል እንዲሁም በህይወትዎ ውስጥ ያሉ በችግር ላይ ያሉ ሰዎችን እንዴት ማገዝ እንደሚችሉ መመሪያ ይሰጣል። |
|
መሰረታዊ ፍላጎቶች |
|
211፣ ወይም 211.org እንደ ምግብ፣ መኖሪያ ቤት፣ የገንዘብ መመሪያ፣ ሱስ፣ የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ትምህርት ወይም ስራ፣ ስሜታዊ ደህንነት እና ሌሎችም ላሉ ወሳኝ የግል ህይወት እገዛ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ 211 ይደውሉ። |
|
ድንገተኛ ሁኔታዎች |
|
911
ለድንገተኛ ጊዜ ወደ 911 ይደውሉ። |
|
የአእምሮ ጤና እና የንጥረ ነገርን አላግባብ መጠቀም |
|
Washington Recovery Help Line (የዋሽንግተን መልሶ ማግኛ እገዛ መስመር)፦ 1-866-789-1511።
በአእምሮ ጤና ስጋቶች እና በንጥረ ነገር አላግባብ መጠቀም ላይ እገዛ ለማግኘት ይደውሉ። |
|
የቤት ውስጥ ጥቃት |
|
National Domestic Violence Hotline (የሀገር ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት የስልክ መስመር)፦ 1-800-799-7233።
እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው የቤት ውስጥ ጥቃት ካጋጠመዎት ይደውሉ። እንዲሁም “start” ብለው ወደ 88788 መላክ ይችላሉ። |
ነፃ የድር ግብዓቶች
Ginger* Emotional Support መተግበሪያ (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ)
Ginger በስማርትፎንዎ ላይ የሚገኝ ነፃ መተግበሪያ ሲሆን ለስሜታዊ ድጋፍና የህይወት መመሪያ 24/7 ግላዊ እና ሚስጥራዊ ስልጠና ይሰጣል።
ለመረጋጋት የሚያግዙ መሣሪያዎች
ለመረጋጋት የሚያግዙ መሣሪያዎች ጭንቀትን ለማርገብና በህይወትዎ ውስጥ የበለጠ መረጋጋትን ለማግኘት የሚያግዙ ተግባራዊ መሣሪያዎችን ያቀርባሉ እና የ6-ሳምንት 6-ሰዓት የቀጥታ የዌቢናር ኮርስ በኩል ይሰራሉ። ይህ ለሁሉም ተንከባካቢዎች ክፍት የሆነ የትምህርት ጥቅም ነው። ተጨማሪ ትምህርት (CE) መስፈርት ላላቸው ተንከባካቢዎች፣ ለመረጋጋት የሚያግዙ መሣሪያዎች መውሰድ የ6 CE ክሬዲቶችን ያሰጥዎታል።[/vc_column_text][vc_tta_tabs][vc_tta_section title=”የራስ እንክብካቤ ማድረጊያ መሣሪያዎች” tab_id=”1671136227253-fb877a00-b77f”][vc_column_text]Find Your Words (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ)
ለራስዎ በተሻለ ሁኔታ እንዲንከባከቡ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለመርዳት፣ እገዛ ለመጠየቅ እና ከልጆችዎ ጋር ስለ ስሜታዊ ደህንነትዎ እንዴት መነጋገር እንደሚችሉ የሚጠቁሙ የኦንላይን ግብዓቶች።
Emotional Support Human
ድጋፍ ለማግኘት እና ሌሎች የስሜታዊ ደህንነት ፈተናዎች እያጋጠሟቸው ያሉትን ለመደገፍ የሚውሉ ግብዓቶች።
American Red Cross Resources for Emotional Support and Grief Counseling (የአሜሪካ ቀይ መስቀል መርጃዎች ለስሜታዊ ድጋፍና የሀዘን ማማከር) (እንግሊዘኛ እና ስፓኒሽ)
በአቅራቢያዎ ያሉ ግብዓቶች እና የድጋፍ ቡድኖች ለሀዘን እና ማጣት ስሜታዊ ድጋፍ እና ምክር ይሰጣሉ።
ለባለሙያ ተንከባካቢዎች የራስ-እንክብካቤ መመሪያ
ተንከባካቢዎች እራስን መንከባከብን እንዲለማመዱ የሚረዱ ምክሮችና ግብዓቶች።
National Institutes of Health Emotional Health Toolkit (ብሔራዊ የጤና ስሜታዊ ጤና መሣሪያ ስብስብ) (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ)
ውጥረትን፣ ጥንቃቄን፣ ስሜትን መቋቋም እና ማጣትን መቋቋምን ጨምሮ ስሜታዊ ደህንነትዎን የሚንከባከቡ ጽሑፎች እና ምክሮች።[/vc_column_text][/vc_tta_section][vc_tta_section title=”የህግ ግብዓቶች” tab_id=”1671136227275-fe0627c5-fe90″][vc_column_text]በኪንግ ካውንቲ የሚኖሩ ከሆነ፣ ሪፈራል ያግኙ (የአስተርጓሚ አገልግሎቶች ሊኖሩ ይችላሉ)፦
- King County Bar Association Lawyer Referral Service (የኪንግ ካውንቲ ጠበቆች ማህበር የህግ ባለሙያ ሪፈራል አገልግሎት)፦ 1-206-267-7010.
የሪፈራል አገልግሎት ለነጻ ወይም ዝቅተኛ ወጭ የህግ ድጋፍ።
ነጻ ስቴት-አቀፍ የህግ ግብዓቶችን ያግኙ፦
- Washington LawHelp።
የነጻ የህግ ድጋፍ ግብዓቶች። - Washington State Bar Associations Directory (የዋሽንግተን ስቴት ጠበቆች ማህበራት ስብስብ)።
በካውንቲ የተደራጁ የስቴት ጠበቆች ማህበራት ስብስብ፣ ብዙዎቹም የጠበቃ ሪፈራል አገልግሎቶች አሏቸው። - Northwest Justice Project።
ነፃ የህግ ድጋፍ ለሰው ልጆች እንደ መኖሪያ ቤት፣ የቤተሰብ ደህንነት፣ የገቢ ዋስትና፣ የጤና እንክብካቤና ትምህርት።
ፈቃድ ያለው ቴራፒስት Resmaa Menakem ለምን ሁላችንም በዘር ጉዳት እንደምንሰቃይ (ነጮችም ጭምር) እና እንዴት መፍታት እንዳለብን ይናገራል።
ለጥቁር ልጃገረዶች ቴራፒ፦ የዘር ጉዳት ተፅዕኖ። (እንግሊዘኛ)
ፈቃድ ያላት የስነ ልቦና ባለሙያዋ ዶ/ር Candice Nicole Hargons ጥቁር ህዝቦችን በዘር ላይ ጉዳትን ለመፍታት እንዲሰሩ ግብዓቶችን ለማስታጠቅ የሰራችውን እና አሁንም እየሰራች ያለችውን ስራ ተናግራለች።
Project Lotus (እንግሊዝኛ)
የኤሽያ አሜሪካውያን ያለምንም መገለል ስሜታዊ ደህንነታቸውን እንዲንከባከቡ እና እንዲናገሩ የሚያስችል የኦንላይን ማህበረሰብ።
Black Emotional and Mental Health Collective (ጥቁር ስሜታዊ እና የአእምሮ ጤና ስብስብ) (እንግሊዝኛ)
በስልጠና እና በትምህርት መርሃግብሮች የዘር እንቅፋቶችን ለስሜታዊ ጤና አጠባበቅ የሚዋጋ ብሔራዊ ድርጅት።[/vc_column_text][/vc_tta_section][/vc_tta_tabs][/vc_column][/vc_row][vc_row][vc_column][vc_column_text]
ግብዓት ፈላጊ/Resource Finder
Resource Finder ለእርስዎ ትክክለኛውን አማራጭ ለማግኘት እገዛን ከፈለጉ፣ የስሜት ጤና ድጋፍን፣ የልጅ እንክብካቤ ግብዓቶችን፣ የህግ እገዛን፣ የእዳ መመሪያን እና ሌሎችንም ጨምሮ ትክክለኛውን የግል ህይወት እርዳታ አገልግሎቶችን ለማግኘት ግብዓት ፈላጊ/Resource Finder ን ይጠቀሙ።
በ SEIU 775 Benefits Group በኩል የጤና ጥቅሞች ላላቸው ተንከባካቢዎች የሚውሉ ግብዓቶች
በ SEIU 775 Benefits Group በኩል የመድን ሽፋን ካለዎት በጤና እንክብካቤ ሽፋንዎ በኩል የስሜት ደህንነት ግብዓቶች ይገኛሉ።**
የጤና እቅድዎ እርስዎ በሚኖሩበት አውራጃ ይወሰናል። ምን አይነት እቅድ እንዳለዎት እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ለማወቅ ይህንን ካርታ ይጠቀሙ።