መሰረታዊ ስልጠና 9

[vc_row][vc_column][vc_column_text]መሰረታዊ ስልጠና 9 በእረፍት ላይ ላሉ ተንከባካቢዎች ስልጠና ያስፈልጋል።

የስልጠናው 9 ሰአት በሙሉ በኦንላይን ሊጠናቀቅ ይችላል። እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ይወቁ እና ስልጠናዎን ከዚህ በታች ያጠናቅቁ። 

መሰረታዊ ስልጠና 9ን ማጠናቀቅ የሚያስፈልጋቸው ሁሉም ተንከባካቢዎች ስለሚወስዱት የሰዓት ብዛት እና የቀነ-ገደቡ መረጃ የያዘ ኢሜይል መቀበል ነበረባቸው። ይህንን ኢሜይል ካላዩ እና ስልጠናዎን ማጠናቀቅ ከፈለጉ፣ እባክዎ ለአባል የመርጃ ማዕከል (MRC) በ 1-866-371-3200 ይደውሉ ወይም በ mrc@myseiubenefits.org ኢሜይል ይላኩ። እነሱ ከሰኞ እስከ አርብ ከ 8 a.m. እስከ 4:30 p.m. ይገኛሉ።

የስልጠናዎ ቀነ-ገደቦች

በኮቪድ-19 ተጽእኖዎች የተነሳ የዋሽንግተን ስቴት ለተንከባካቢ ስልጠና መስፈርቶች ቀነ-ገደቡን አራዘመ። የማህበራዊ እና የጤና አገልግሎቶች መምሪያ (DSHS) በተቀጠሩበት ቀን መሰረት አዲስ ቀነ-ገደብ አዘጋጅቷል።

አስፈላጊውን ስልጠና በቀነ-ገደብዎ ካልጨረሱ፣ እንደ ተከፋይ ተንከባካቢ መስራትዎን መቀጠል አይችሉም።

የተቀጠሩበት ወይም ዳግም የተቀጠረቡት ቀን መሰረታዊ ስልጠና መጠናቀቅ ያለበት በ
ከ 8/17/2019 እስከ 9/30/2020 10/31/2022
ከ 10/1/2020 እስከ 4/30/2021 1/31/2023
ከ 5/1/2021 እስከ 3/31/2022 4/30/2023
4/1/2022 እስከ 9/30/2022 8/31/2023
[/vc_column_text][/vc_column][/vc_row][vc_row][vc_column][vc_tta_tabs][vc_tta_section title=”መመዝገብ” tab_id=”1658515685400-8097d7c3-f430″][vc_column_text]

የኦንላይን መለያዎን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ 

  1. ወደ myseiu.be/online22 ይሂዱ። መለያ መፍጠር አያስፈልግዎትም።
  2. ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገቡ የሚከተለውን መረጃ ይጠቀሙ፦
    • ለኢሜይልዎ፣ ሲቀጠሩ የሰጡትን የኢሜይል አድራሻ ይጠቀሙ።
    • ለይለፍ ቃል፣ Summer2022 ይተይቡ።
  3. ልክ እንደገቡ የይለፍ ቃልዎን ያዘምኑ እና የእውቂያ መረጃዎን ያረጋግጡ።
  4. ከገቡ በኋላ፣ ካሉት ኮርሶች ለመምረጥ ወደ ካታሎግ ይሂዱ።

እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ፣ ለዝርዝር መመሪያዎች የመሰረታዊ ስልጠና 9 መመሪያን ይመልከቱ።[/vc_column_text][/vc_tta_section][vc_tta_section title=”ስልጠናዎን ማጠናቀቅ” tab_id=”1658515685386-a46f8dad-e88a”][vc_column_text]ስልጠናዎን ለማጠናቀቅ የ 9 ሰዓታት የኦንላይን ኮርሶችን መውሰድ ያስፈልግዎታል። እነዚህን ኮርሶች ከካታሎግ ገጽ መምረጥ ይችላሉ።

ሊወስዷቸው የሚችሏቸው ኮርሶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ 

  • መጀመሪያ ነገሮች በመጀመሪያ – እራስዎን መንከባከብ (2 ሰዓ)
  • የደንበኞች አገልግሎት ችሎታዎች (1 ሰዓ)
  • ወደ አመጋገብ መሰረታዊ ነገሮች መመለስ (3 ሰዓ)
  • ሥር የሰደደ ስቃይ ያለበትን ደንበኛን መርዳት (2 ሰዓ)
  • መውደቅ እና ውድቀትን መከላከል (1 ሰዓ)
  • በቀኝ እና በግራ ጎን ስትሮክ መካከል ያለው ልዩነት (3 ሰዓ)
  • እንዴት ታላቅ የቡድን አባል መሆን እንደሚቻል (1 ሰዓ)
  • በቂ ZZZs ማግኘት – የእንቅልፍ አስፈላጊነት (1 ሰዓ)
  • ከአረጋውያን ጋር በመነጋገር መተማመንን መፍጠር (2 ሰዓ)
  • በአዛውንት ደንበኛ የንጥረ ነገር አላግባብ መጠቀም እና ሱስ (2 ሰዓ)
  • በአዛውንት ደንበኛዎ ውስጥ የመንፈስ ጭንቀትን ማወቅ (2 ሰዓ)
  • በመሞት ላይ ላለ ግለሰብ የሚደረግ እንክብካቤ (4 ሰዓ)
[/vc_column_text][/vc_tta_section][vc_tta_section title=”የቋንቋ ድጋፍ” tab_id=”1662490148398-ac0835c5-3d22″][vc_column_text]

ይህ ኮርስ በአሁኑ ጊዜ የሚሰጠው በእንግሊዝኛ ብቻ ነው። በሌላ ቋንቋ ለመውሰድ እገዛ ከፈለጉ፣ የማህበረሰብ አስተርጓሚ መጠቀም ይችላሉ።

የማህበረሰብ አስተርጓሚ ማለት ደንበኛዎ ያልሆነ እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ጓደኛ ወይም ዘመድ ነው።

[/vc_column_text][/vc_tta_section][vc_tta_section title=”ጥያቄዎች አሉዎት?” tab_id=”1658515845399-e4968ea6-000c”][vc_column_text]

ጥያቄዎች አሉዎት?

ስልጠናዎን ለመመዝገብ እና ለማጠናቀቅ እርዳታ ከፈለጉ፣ የመሰረታዊ ስልጠና 9 መመሪያን ይመልከቱ።

ለተጨማሪ ድጋፍ፣ የአባል መርጃ ማዕከልን (MRC) ያነጋግሩ።

  • ስልክ ቁጥር፦ 1-866-371-3200፣ ከሰኞ–ዓርብ፣ 8 a.m.–4:30 p.m.
  • ኢሜይል: mrc@myseiubenefits.org
  • የመጀመሪያ ቋንቋዎ እንግሊዘኛ ካልሆነ፣ በMRC ውስጥ ያሉ ተወካዮች በቋንቋዎ ከእርስዎ ጋር ሊነጋገሩ ይችላሉ።
[/vc_column_text][/vc_tta_section][/vc_tta_tabs][/vc_column][/vc_row]