ወደ እንክብካቤ መስጫ እንኳን በደህና መጡ!

Ver en español | 查看中文 | 한국어로 보기 | Посмотреть на русском | Xem bằng tiếng việt | عربى | Soomaali

ወደ እንክብካቤ መስጫ እንኳን በደህና መጡ! እንክብካቤ የመስጠት ስራዎን ሲጀምሩ፣ ለእንክብካቤ ሰጪ ያሉትን ጥቅማ ጥቅሞች ሁሉ መጠቀምዎን ያረጋግጡ፣ ለምሳሌ:

  • የትምህርት ጥቅሞች እና የሙያ እድገት ዕድሎች።
  • ብቁ ለሆኑ ተንከባካቢዎች በወር $25 ብቻ የሚጠይቅ ከፍተኛ ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ።
  • አሰሪዎ የሚያበረክተው የጡረታ እቅድ።
  • እንደ Reebok ካሉ ታዋቂ ምርቶች የሚያንሸራትት ነገርን መቋቋም የሚችሉ ነፃ ጫማዎች።
  • ውጥረትን ለመቀነስ የሚያግዙ ነፃ የራስ-እንክብካቤ መገልገያዎች። 
  • እና ብዙ ተጨማሪ።

ስለ የእርስዎ ትምህርትጤናጡረታ እና ስራ-ማዛመድ ጥቅማጥቅሞችን ከዚህ በታች ያንብቡ።


ትምህርት

ለደንበኛዎ ወይም ቤተሰብዎ ከፍተኛ ጥራት ያለው እንክብካቤ እንዲሰጡ የሚያግዙዎትን የትምህርት ጥቅማጥቅሞች ያገኛሉ።

እንክብካቤ ሰጪ እንደሆኑ የትምህርት ጥቅማ ጥቅምዎችዎ ይጀምራሉ። ምን ዓይነት ስልጠና እንደሚያስፈልግዎ የበለጠ ይወቁ። እንደ መደበኛ የቤት ውስጥ እንክብካቤ ሰጪ (HCA) ማረጋገጫ ለማግኘት ካሰቡ፣ ለማረጋገጫ ስለሚወስዷቸው እርምጃዎች ማወቅ ይችላሉ። 

እገዛ ከፈለጉ፣ Peer Mentors (የአቻ ለአቻ አሠልጣኞች) ከብዙ ዓመታት ልምድ ጋር ፈቃድ የተሰጣቸው ተንከባካቢዎች ናቸው ስለሆነም በመማር ሂደትዎ፣ በ HCA የምስክር ወረቀት ሂደት እና በሌሎችም በመምራት ረገድ ሊረዱዎት ይችላሉ። ስለ Peer Mentors (የአቻ ለአቻ አሠልጣኞች) የበለጠ ይወቁ

ስለ ትምህርት ጥቅሞችዎ የበለጠ ይወቁ። 


ጤና

የጤና እንክብካቤ ሽፋን በወር በ $25 ብቻ ለብቁ እንክብካቤ ሰጪዎች ይገኛል! ለተከታታይ 2 ወራት በወር 80 ሰዓት ሲሰሩ ከፍተኛ ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ ማግኘት ይችላሉ። ጥቅማ ጥቅሞቹ የህክምና፣ የጥርስ፣ የሀኪም ማዘዣ፣ የስሜታዊ ጤንነት፣ የእይታ፣ የመራባት እና የአጥንት ህክምና ጥቅሞችን እንዲሁም የነፃ የመጀመሪያ እንክብካቤ ሀኪም ጉብኝቶችን ያካትታሉ። ስለ ብቁነት የበለጠ ይወቁ እና ዛሬ ያመልክቱ። 

ከጤና እንክብካቤ ሽፋን በተጨማሪ፣ ነፃ ጥቅሞችን ማለትም እንደ Tools for Calm (ለመረጋጋት የሚጠቅሙ መገልገያዎች)፣ Resource Finder (ግብዓት ፈላጊ)፣ Ginger smartphone app (ጊንገር ስማርትፎን መተግበሪያ)፣ Caregiver Kicks (ለአሳዳጊዎች ነፃ ጫማ) እና ሌሎችም የመሳሰሉ ማግኘት ይችላሉ። 

ስለ ሁሉም የጤና ጥቅሞችዎ የበለጠ ይወቁ። 

ጡረታ

የ SEIU 775 ደህንነቱ የተጠበቀ የጡረታ እቅድ ለተንከባካቢዎች ልማድ የመጀመሪያው ነው። ጡረታ ሲወጡ ተጨማሪ የገንዘብ ዋስትና ለእርስዎ ለመስጠት ለማገዝ የተዘጋጀ ነው።

ተንከባካቢዎች የ 6 ወር ተሳትፎ መስፈርቱን ካሟሉ በኋላ በራስ-ሰር በእቅዱ ውስጥ ተመዝግበዋል። ጡረታ ሲወጡ የጡረታ ድጎማ መቀበልን መጀመር ይችላሉ። 

ስለ ጡረታዎ ጥቅሞችዎ የበለጠ ይወቁ

 

ስራ-ማዛመድ

ተጨማሪ ሰዓታት ይፈልጋሉ? በ Carina በኩል ትክክለኛውን ደንበኛ ያግኙ። Carina ደህንነቱ የተጠበቀ የኦንላይን መለያዎችን እና መልዕክቶችን በመጠቀም ተንከባካቢዎችን ከደንበኞች ጋር የሚዛመድ ድረገፅ ነው። Carina በአካባቢዎ ውስጥ የመጠባበቂያ እንክብካቤን እንዲያገኙም ይረዳዎታል። 

ስለ Carina የበለጠ ይወቁ