Open Enrollment (አመታዊ የምዝገባ ጊዜ ለጤና ሽፋን) ከጁላይ 1-20

በመድን ሽፋንዎ ላይ ይመዝገቡ ወይም ለውጦችን ያድርጉ!

Ver en español | 查看中文 | 한국어로 보기 | Посмотреть на русском | Xem bằng tiếng Việt | عربى | Soomaali

$10 የጥርስ ህክምና ለእርስዎ ጥገኛዎች

በወር 120 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ ከሰሩ፣ አሁን ጥገኞችዎን በወር $10 ብቻ በመክፈል በጥርስ ህክምና ሽፋን መመዝገብ ይችላሉ*! 

 

ጁላይ 1-20፦ በዚህ ዓመት የእርስዎ ብቸኛ እድል

Open Enrollment (ዓመታዊ የምዝገባ ጊዜ ለጤና ሽፋን) በጤና እንክብካቤ መድን ሽፋን (ብቁ ከሆኑ)፣ ጥገኛ ለማከል እና/ወይም በመድን ሽፋንዎ ላይ አማራጭ ለውጦችን ለማድረግ (ከተመዘገቡ) የሚችሉበት አመታዊ እድልዎ ነው።

 • አሁን ብቁ ከሆኑ እና በመድን ሽፋን ከተመዘገቡ፣ የመድን ሽፋንዎ ኦገስት 1 ይጀምራል።
 • አሁን ብቁ ካልሆኑ ነገር ግን የመድን ሽፋኑን የማግኘት ፍላጎት ካለዎት፣ አሁንም የተሟላ የጤና ጥቅማጥቅሞች ማመልከቻውን እስከ ጁላይ 20 ድረስ ማስገባት አለብዎት። ብቁ ሲሆኑ የመድን ሽፋንዎ ይጀምራል።
 • አስቀድመው የተመዘገቡ ከሆኑ፣ ጥገኛን ለማከል ወይም የጥርስ ህክምና መድን ዕቅድዎን ለመቀየር ካልፈለጉ በስተቀር እርምጃ መውሰድ አያስፈልግዎትም።

በወር 80 ወይም ከዚያ በላይ ሰዓታት በተከታታይ 2 ወራት ሲሰሩ በ SEIU 775 Benefits Group በኩል ለግል የጤና እንክብካቤ መድን ሽፋን ብቁ ይሆናሉ። በወር 120 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ ከሰሩ፣ ጥገኛዎን በወር $10 ብቻ በመክፈል በጥርስ ህክምና መድን ሽፋን ማስመዝገብ ይችላሉ*!

ስለ ብቁነት ጥያቄዎች ካሉዎት፣ በ 1-877-606-6705 ወደ SEIU 775 Benefits Group የደንበኛ አገልግሎት ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ8 am. እስከ 6 p.m የፓስፊክ አቆጣጠር መደወል ይችላሉ።

 

በጁላይ 20 ወይም ከዚያ በፊት የጤና መድን ጥቅማ ጥቅሞች ማመልከቻውን በኦንላይን Health: My Plan ወይም በፖስታ ይሙሉት እና መልሰው ያስገቡት።

የተጠናቀቀውን ማመልከቻ በጁላይ 20 ወይም ከዚያ በፊት ካስገቡ የአዲስ ተመዝጋቢዎች መድን ሽፋን ኦገስት 1 ይጀምራል። ቀድሞውኑ ተመዝግበው ግን ምንም እያደረጉ ካልሆነ፣ አሁን የሚቀበሉትን ሽፋን መቀበልዎን ይቀጥላሉ። በሚቀጥለው ጊዜ በመድን ሽፋንዎ ላይ ለውጦችን ማድረግ የሚችሉት በሚቀጥለው Open Enrollment (ዓመታዊ የምዝገባ ጊዜ) (ጁላይ 2023) ወይም ብቁ የሆነ የህይወት ክስተት (QLE) ካለዎት ነው።

የእርስዎ ጥገኛ መድን ሽፋን መጀመሪያ ቀን የእርስዎ ጥገኛ ማረጋገጫ በደረሰው መሰረት ይለያያል።

 

የሚያገኙት ነገር

ለ25$ በወር፣ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያገኛሉ፡

 • ነፃ ተቀዳሚ እንክብካቤ የሀኪም ጉብኝቶች
 • ሜዲካል
 • የጥርስ ሕክምና
 • ኦርቶዶንቲያ
 • የማየት ችሎታ
 • መስማት ችሎታ
 • መካንነት
 • በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት
 • የስሜት ድጋፍ

ለእርስዎ ብቻ የተዘጋጁ ተጨማሪ ጥቅሞች
የስሜታዊ ጤንነትዎ ልክ እንደ አካላዊ ጤንነትዎ አስፈላጊ ነው። የመድን ሽፋን የሳይኮቴራፒ፣ የመድሃኒት፣ የቡድን ህክምና እና ተጨማሪና አማራጭ መድሃኒቶች እና ሌሎች ለተንከባካቢዎች የተነደፉ ጥቅሞችን ያጠቃልላል፦ 

 

እንዴት መመዝገብ ወይም ለውጦችን ማድረግ እንደሚቻል

ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 20፣ ለመመዝገብ ወይም ሽፋንዎን ለመቀየር 2 አማራጮች አሉ። ማመልከቻዎ መስተናገድ እንዲችል እስከ ጁላይ 20 ድረስ መግባት አለበት።

በኦንላይን በ Health: My Plan

ይመዝገቡ፣ ስለጤና ጥቅሞችዎ መረጃን ለማግኘት ወደሚገቡበት ድረገፅ Health: My Plan በቀላሉ በመጠቀም ጥገኛ ያክሉ እና/ወይም ለውጦችን ያድርጉእርስዎ Health: My Plan  ገና ካልተጠቀሙ መግቢያ መፍጠር ያስፈልግዎ ይሆናል። 

ለሚከተሉት ጉዳዮች Health: My Plan  ን መጠቀም ይችላሉ፦

 • በጥቅሞች ይመዝገቡ፣ ጥገኛ ያክሉ እና/ወይም Open Enrollment (በዓመታዊ የምዝገባ ጊዜ) (ወይም ብቁ የህይወት ክስተት፣ ወይም QLE ካለዎት) አሁን ባለው የመድን ሽፋንዎ ላይ ለውጦችን ያድርጉ።
 • ለጥገኛ ማረጋገጫ ሰነድ ያስገቡ።
 • ሰአታትዎን እና ብቁነትዎን ይመልከቱ።
 • የእርስዎን ጥቅማጥቅሞችን እና ሽፋኑን በተመለከተ መረጃ ያግኙ።
 • ቅጾች፣ የእቅድ ሰነዶች፣ ራስዎ-የሚከፍሉት ክፍያ እና የክፍያ ታሪክን ያግኙ።

መግቢያዎ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ይወቁ።

  በደብዳቤ

ለመሙላት እና ለማስገባት ጥቅል እና የጤና ጥቅሞች ማመልከቻ (ከጁን አጋማሽ እስከ መጨረሻ ድረስ ተልኳል) ተልኮልዎታል። ፖስታ መላክ አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን ማመልከቻዎን ማስገባት ቀላል ነው! ከመመለሻ አድራሻዎ ጋር አድርገው በመልዕክት ይላኩት፦

SEIU 775 Benefits Group
PO Box 24811
Seattle, WA 98124

ማመልከቻዎን ካስገቡ በኋላ በ45 ቀናት ውስጥ የምዝገባ ማረጋገጫ ካላገኙ ወይም ለውጦችን ካቀዱ፣ ለ SEIU 775 Benefits Group የደንበኞች አገልግሎት በ 1-877-606-6705 ይደውሉ።

 

ጥያቄዎች አሉዎት?

ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም የቋንቋ እገዛ ከፈለጉ፣ ለ SEIU 775 Benefits Group የደንበኞች አገልግሎት በ 1-877-606-6705 ይደውሉ።

 

*ለኤጀንሲ አቅራቢዎች (AP) እና CDWA የግለሰብ አቅራቢዎች (IP) በKPWA HMO፣ KPNW ወይም Aetna ላይ ብቻ። በአሁኑ ጊዜ በKPWA POS ዕቅድ ውስጥ ከተመዘገቡ እና ለጥገኛዎ $10 የጥርስ ህክምና ማግኘት ከፈለጉ፣ የህክምና ዕቅድዎን መለወጥ ያስፈልግዎታል። ለእገዛ ወደ 877-606-6705 ይደውሉ።

 

Open
Enrollment
Packet (ዓመታዊ የምዝገባ ጥቅሎች)

Open Enrollment Packet (ዓመታዊ የምዝገባ ጥቅል)

የ2022 Open Enrollment packets (ዓመታዊ የምዝገባ ጥቅሎችን) ይመልከቱ።
የህክምና መድን እቅድዎ በዚፕ ኮድዎ መሰረት ተመድቦለታል። ከደልታ ዴንታል ወይም ዊላሜቲ ዴንታል ለጥርስ ህክምናዎ መምረጥ ይችላሉ። ለመድን ሽፋን ብቁ ከሆኑ ወይም ከተመዘገቡ፣ እነዚህን ፓኬቶች በመይል መቀበል ይችላሉ።

Aetna
KPNW
KPWA HMO
KPWA POS