የጥገኛ መድን ሽፋን

Ver en español | 查看中文 | 한국어로 보기 | Посмотреть на русском | Xem bằng tiếng Việt | عربى | Soomaali

$10 የጥርስ ህክምና ለእርስዎ ጥገኛዎች*

ከዚህ አመት ጀምሮ፣ በወር 120 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ ከሰሩ፣ ጥገኛ ልጆችዎን በወር $10 ብቻ በመክፈል በጥርስ ህክምና ሽፋን መመዝገብ ይችላሉ።

ጥገኛን ወደ ሽፋንዎ ሲያክሉ አሁን የሚመርጧቸው 2 አማራጮች አሉዎት፦

የእርስዎን ጥገኞች (ዎች) ሲያስመዘግቡ፣ ከታች ካሉት የጥገኛ መድን ሽፋን አማራጮች ውስጥ አንዱን መምረጥ ያስፈልግዎታል። ይህንን ለማድረግ፣ መመሪያዎቹን በጤና ጥቅሞች ማመልከቻ ላይ ወይም በኦንላይን Health: My Plan ን በመጠቀም ይከተሉ። እገዛ ይፈልጋሉ? ወደ 1-877-606-6705 ይደውሉ።

 

 

የ80 ሰዓት ምርጫ

በወር ከ80-119 ሰዓታት ለሚሰሩ ተንከባካቢዎች በጣም የተሻለ። በወር 80 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ እስኪሰሩ ድረስ የጥገኛዎ መድን ሽፋን አይጀምርም።

 • ሙሉ የህክምና እና የጥርስ ህክምና በሙሉ ፕሪሚየም ወጪ (በወር $686-$786፣ እና ለመድን ሽፋንዎ $25 በወር)።
 

የ120 ሰዓት ምርጫ (የ $10 የጥገኛ ጥርስ ህክምናን ያካትታል)

በወር ከ120 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ ለሚሰሩ ተንከባካቢዎች በጣም የተሻለ። በወር 120 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ እስኪሰሩ ድረስ የጥገኛዎ መድን ሽፋን አይጀምርም።

 • ሙሉ የህክምና እና $10 የጥርስ ህክምና (አጠቃላይ በወር $628-$697 ለጥገኛዎ እና ለመድን ሽፋንዎ በወር $25)።
 • ወይም የጥርስ ህክምና ሽፋን በወር $10 ብቻ (በተጨማሪም በወር $25 ለመድን ሽፋንዎ)።

ወርሃዊ ክፍያዎ ካልደረሰ ወይም ሰአታትዎ ለእርስዎ ጥገኛ ሽፋን አማራጭ ከሚያስፈልገው በታች ከቀነሰ፣ ጥገኞችዎ የመድን ሽፋን ያጣሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመዘገቡ ወይም Open Enrollment (በዓመታዊ የምዝገባ) ጊዜ (በየጁላይ 1-20) የጥገኝነት መድን ሽፋን ምርጫዎን መምረጥ ወይም መለወጥ ብቻ ይችላሉ። እንደ ልጅ መውለድ ያለ ብቁ የሆነ የህይወት ክስተት ካለዎት አሁንም ጥገዎን ወደ መድን ሽፋንዎ ማከል ይችላሉ። ግን፣ የእርስዎን ጥገኛ መድን ሽፋን አማራጭ መለወጥ ከፈለጉ፣ እስከሚቀጥለው Open Enrollment (ዓመታዊ የምዝገባ ጊዜ) ድረስ መጠበቅ ሊኖርብዎ ይችላል።

*በወር 120 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ ለሚሰሩ እና በKPWA HMO፣ Aetna እና KPNW ዕቅዶች ላይ ብቻ ለሆኑ ተንከባካቢዎች የሚገኝ። በKPWA POS ዕቅድ ውስጥ ከተመዘገቡ እና ለጥገኛዎ $10 የጥርስ ህክምና መድን ሽፋን ማግኘት ከፈለጉ፣ የህክምና ዕቅድዎን መለወጥ ያስፈልግዎታል። ለእገዛ ወደ 1-877-606-6705 ይደውሉ።

 

ጥገኛን እንዴት መመዝገብና ማረጋገጥ እንደሚቻል

በሽፋንዎ ላይ ጥገኛን ለመመዝገብና ከእነሱ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ለማረጋገጥ ብዙ እርምጃዎች አሉ። ይህንን በኦንላይን በ Health: My Plan ወይም በመልዕክት ማድረግ ይችላሉ።

ጥገኛ በኦንላይን ይመዝገቡ  ጥገኛን በፋክስ ይመዝገቡ
 • የጤና ጥቅማጥቅሞች ማመልከቻ ላይ ያለውን የጥገኛ ክፍል ሞልተው (እስከ ጁላይ 20 ድረስ Open Enrollment ወቅት) በጤና ጥቅማጥቅሞች ማመልከቻ ላይ ወዳለው አድራሻ ይላኩ።
 • ማመልከቻዎን በጤና ጥቅማጥቅሞች ማመልከቻ ላይ ወዳለው አድራሻ በላኩ በ60 ቀናት ውስጥ ከጥገኛዎ(ችዎ) ጋር ያለዎትን ግንኙነት የሚያረጋግጥ ሰነድ ያስረክቡ።
 • በደመወዝ ቅነሳ መክፈል ይጀምሩ።

ስለ ጥገኝነት ማረጋገጫ ተጨማሪ ዝርዝሮች፦

 • የጥገኛ የማረጋገጫ ሰነድዎ ከማመልከቻዎ ጋር ማስገባት ይችላሉ፣ ግን ማመልከቻዎ ከደረሰ በኋላ ለማስረከብ 60 ቀናት አለዎት። የጥገኛን ማረጋገጫ እስኪልኩ ድረስ ማመልከቻዎ አልተጠናቀቀም። 
  • የጤና ጥቅሞችን ማመልከቻዎን ካስገቡ በኋላ የጥገኝነት ማረጋገጫ ሰነድዎን ለመላክ ከመረጡ፣ ከማመልከቻዎ ጋር እንዲመሳሰል ስምዎን እና የልደት ቀንዎን አብረው ማካተትዎን ያረጋግጡ።
 • ዋናውን ሰነድ ሳይሆን ቅጂውን መላክዎን ያረጋግጡ።

 

በእኔ መድን ሽፋን ላይ ማንን መጨመር እችላለሁ?

ብቁ የሆኑ ልጆችን (እስከ 26ኛ የልደት በዓላቸው) በጥገኛ መድን ሽፋን መመዝገብ ይችላሉ። ጥገኞ(ዎችዎን) ለማስመዝገብ ከመረጡ፣ ከእነሱ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ማረጋገጥ ያስፈልግዎታል። ብዙ ብቁ የሆኑ ልጆችን በመድን ሽፋን መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን ምንም ያህል ልጆች ቢመዘገቡ ወርሃዊ ወጪዎ አንድ አይነት ይሆናል።

 • ለምሳሌ፦ 2 ልጆችን በ120 ሰዓትት ምርጫ ለ1$10 የጥርስ ህክምና መድን ሽፋን ብቻ ካስመዘገቡ፣ የወርሃዊ ጥገኛ መድን ሽፋን ዋጋ ለሁለቱም ጥገኞች በድምሩ $10 ይሆናል።

ከዚህ በታ ያለው ብቁ የሆኑ የልጆች ጥገኞች ዝርዝር ነው። ለእያንዳንዱ አይነት ጥገኛ እንደ የትኞቹን ሰነዶች እንደ ማረጋገጫ አድርገው መጠቀም እንደሚችሉ ለማየት “+” ን ጠቅ ያድርጉ። ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም ጥገኛ ልጅ ለማስመዝገብ እገዛ ከፈለጉ፣ ወደ SEIU 775 Benefits Group የደንበኞች አገልግሎት በ 1-877-606-6705 ከ 8 a.m. እስከ 6 p.m.፣ ከሰኞ እስከ አርብ ይደውሉ።

 

የውልደት ልጅዎን እንደ ጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ዝርዝር እነሆ፦

 • የሁሉንም ወላጆች ስም ያካተተ በመንግስት የተሰጠ የልደት ምስክር ወረቀት። 
 • ልጁን(ልጆቹን) እንደ ጥገኛ(ኞች) ያካተተ እና እንደ ወንድ ወይም ሴት ልጅ የተዘረዘረው በጣም የቅርብ ጊዜ የፌዴራል የግብር ተመላሽ። የፋይናንስ መረጃን መደበቅዎን ያረጋግጡ። 
 • የህፃኑ ዱካዎች ያሉበት የሆስፒታል የምስክር ወረቀት። ተመዝጋቢው ይህም የወላጅ፣ የተመዝጋቢው የትዳር አጋር ወይም የተመዝጋቢው በመንግስት የተመዘገበ የቤት ውስጥ ባልደረባ ስም ማሳየት አለበት። 
 • በፍርድ ቤት የታዘዘ የወላጅነት እቅድ። 
 • ብሄራዊ የህክምና ድጋፍ ማስታወቂያ። 
 • የመከላከያ ምዝገባ ብቁነት ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት (DEERS) ምዝገባ። 
 • በአሜሪካ መንግስት የተሰጠ ህጋዊ J-2 ቪዛ።

የጉዲፈቻ ልጅዎን እንደ ጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ዝርዝር እነሆ፦

 • የልደት የምስክር ወረቀት ወይም የጉዲፈቻ የምስክር ወረቀት። 
 • ልጁን(ልጆቹን) እንደ ጥገኛ ያካተተ እና እንደ ወንድ ወይም ሴት ልጅ የተዘረዘረው በጣም የቅርብ ጊዜ የፌዴራል የግብር ተመላሽ። የፋይናንስ መረጃዎን መደበቅዎን ያረጋግጡ። 
 • የጉዲፈቻ የምስክር ወረቀት ወይም ድንጋጌ። ተመዝጋቢው ይህም የወላጅ፣ የተመዝጋቢ የትዳር አጋር ወይም የተመዝጋቢው በመንግስት የተመዘገበ የቤት ውስጥ ባልደረባ ስም ማሳየት አለበት። 
 • በፍርድ ቤት የታዘዘ የወላጅነት እቅድ። 
 • ብሄራዊ የህክምና ድጋፍ ማስታወቂያ። 
 • የመከላከያ ምዝገባ ብቁነት ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት (DEERS) ምዝገባ። 
 • በአሜሪካ መንግስት የተሰጠ ህጋዊ J-2 ቪዛ። 

የእንጀራ ልጅዎን እንደ ጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ዝርዝር እነሆ፦

 • የልደት የምስክር ወረቀት እንዲሁም ደግሞ በመንግስት የተሰጠ የጋብቻ የምስክር ወረቀት እና ባለፉት 2 ዓመታት ውስጥ ከባለቤትዎ ጋር የተዘረዘረበት የጋራ ባለቤትነት ማረጋገጫ (የሞርጌጅ መግለጫዎች፣ የባንክ መግለጫዎች፣ የክሬዲት ካርድ መግለጫዎች፣ የሊዝ/ኪራይ ስምምነቶች)። 
 • ልጁን(ልጆቹን) እንደ ጥገኛ ያካተተ እና እንደ ወንድ ወይም ሴት ልጅ የተዘረዘረው በጣም የቅርብ ጊዜ የፌዴራል የግብር ተመላሽ (የፋይናንስ መረጃዎን መደበቅዎን ያረጋግጡ)። 
 • በፍርድ ቤት የታዘዘ የወላጅነት እቅድ። 
 • ብሄራዊ የህክምና ድጋፍ ማስታወቂያ። 
 • የመከላከያ ምዝገባ ብቁነት ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት (DEERS) ምዝገባ። 
 • በአሜሪካ መንግስት የተሰጠ ህጋዊ J-2 ቪዛ።

ህጋዊ ሞግዚት ያለብዎትን ልጅ እንደ ጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ዝርዝር እነሆ፦

 • ህጋዊ የአሳዳጊነት ሁኔታን የሚያሳይ የክልል ወይም ፌዴራል መንግስት የህግ ሰነዶች። 
 • ልጁን(ልጆቹን) እንደ ጥገኛ ያካተተ እና እንደ ወንድ ወይም ሴት ልጅ የተዘረዘረው በጣም የቅርብ ጊዜ የፌዴራል የግብር ተመላሽ። የፋይናንስ መረጃዎን መደበቅዎን ያረጋግጡ።
 • በፍርድ ቤት የታዘዘ የወላጅነት እቅድ። 
 • ብሄራዊ የህክምና ድጋፍ ማስታወቂያ። 
 • የመከላከያ ምዝገባ ብቁነት ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት (DEERS) ምዝገባ። 
 • በአሜሪካ መንግስት የተሰጠ ህጋዊ J-2 ቪዛ። 

የማደጎ ልጅዎን እንደ ጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ዝርዝር እነሆ፦

 • ዋናው የማደጎ ልጅ ማረጋገጫ እና የልጁ መደበኛ እና ከፍተኛ ድጋፍ ሰነዶች ቅጂ። 
 • ልጁን(ልጆቹን) እንደ ጥገኛ ያካተተ እና እንደ ወንድ ወይም ሴት ልጅ የተዘረዘረው በጣም የቅርብ ጊዜ የፌዴራል የግብር ተመላሽ። የፋይናንስ መረጃዎን መደበቅዎን ያረጋግጡ። 
 • በፍርድ ቤት የታዘዘ የወላጅነት እቅድ። 
 • ብሄራዊ የህክምና ድጋፍ ማስታወቂያ። 
 • የመከላከያ ምዝገባ ብቁነት ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት (DEERS) ምዝገባ። 
 • በአሜሪካ መንግስት የተሰጠ ህጋዊ J-2 ቪዛ።

የቤት ውስጥ አጋርዎን ልጅዎን እንደ ጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ዝርዝር እነሆ፦

 • በመንግስት የተሰጠ የልደት የምስክር ወረቀት፤ የቤት ውስጥ አጋር ስም ያካትታል። 
 • የፍርድ ቤት ውሳኔ የቤት ውስጥ አጋርን እንደ ህጋዊ ሞግዚት እንዲሰየም ያዛል። 
 • ልጁን(ልጆቹን) እንደ ጥገኛ ያካተተ እና እንደ ወንድ ወይም ሴት ልጅ የተዘረዘረው በጣም የቅርብ ጊዜ የፌዴራል የግብር ተመላሽ። የፋይናንስ መረጃዎን መደበቅዎን ያረጋግጡ። 
 • በፍርድ ቤት የታዘዘ የወላጅነት እቅድ። 
 • ብሄራዊ የህክምና ድጋፍ ማስታወቂያ። 
 • የመከላከያ ምዝገባ ብቁነት ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት (DEERS) ምዝገባ። 
 • በአሜሪካ መንግስት የተሰጠ ህጋዊ J-2 ቪዛ።

**የእንጀራ ልጅዎን ወይም የቤት ውስጥ አጋርዎን ልጅዎን እያስመዘገቡ ከሆነ፣ ተጨማሪ ወረቀቶችን መሙላት ሊኖርብዎ ይችላል። በ 1-877-606-6705፣ ከ 8 a.m. እስከ 6 p.m. የፓስፊክ ሰዓት አቆጣጠር፣ ሰኞ-አርብ ለ SEIU 775 Benefits Group ለእገዛ ይደውሉ።